ልቤ የደነደነ ነው። ኃጢአቴን ተናዝዣለው። ግን የጸጸት ስሜት አልተሰማኝም። ቀኖና ብጨርስ መቁረብ አልችልም "ያልተጸጸተ አይቀበል" በሚለው? እኔ ፍቅረ እግዚአብሔር የሚጨምሩ ነገሮች ላይ ባተኩር ጸጸትን እርሱ ወደፊት ይሰጠኛል ብዬ ብቆርብ ስህተት ነው?
Oct 18, 2025ለመጸጸት መፍትሔ/መንገዶች :- ➢ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ቃሉን በደምብ መረዳት ቤተክርስቲያን/ጉባኤ መሄድ መማር ያኔ ቃሉ በስራችን እንድንጸጸት ያደርጋል ➢ ኃጢአትን ስንሰራው/እንደሰራነው ንስሐ ሳልገባ ብሞትስ ብሎ ማሰብ መዝ 50:25 ➢ የሰራዉን ስህተት/ኃጢአት ከተለያየ አንግል ማየት/ማስተያየት ➢ እግዚአብሔር ትዕግስተኛ እና መሐሪ እንደሆነ ማሰብ ➢ እግርን ጆሮን እና አይንን ብሎም ልብን ከሐጥያቱ ማራቅ ያን ሐጥያት ማሰብ ማሰላሰል ሳይሆን በዛ ሐጥያት ፈጣሪን ምነኛ እንደበደልን ማሰብ እናም ወደ ፈጣሪ መቅረብ ሁሌም ፈጣሪን ማሰብ ➢ ወደ ቤተክርስቲያን ማዘውትር ➢ መንፈሳዊ መፅሐፎችን ማንብብ ፊልምም ቢሆን መንፈሳዊ የሆኑ ፊልሞችን መከታተል ለምሳሌ በዚህ ህይወት ውስጥ ሆነው በንስሐ አልፈው ለቅድስና የበቁትን ማየት (ቅዱሱ ሙሴ ጸሊም፣ግብፃዊቷ ማርያም፣ቅዱስ ቆጵርያኖስ እና ቅድስት ዮስቲና...) ከዛ ያኔ ለውጡን በእርግጠኝነት በደምብ ማየት ይቻላል። በእርግጠኝነት ጸጸት ውስጣችን አለ ሰይጣን ስላደበዘዘብን፣እንዳይሰማን ስላደረገብን፣ኖርማል ስላስመሰለብን ነው እንጂ በመጥፎው ስራ የሚኮራ የለም የሚያፍር እንጂ ያ እፍረት ደሞ ፀፀት ነው ስለዚህ ያደበዘዘብን የጸጸት ስሜት በማጉላት እነዛን መፍትሔዎች በመጠቀም ሰይጣንን ማሸነፍና ወደ ንስሐ መግባት አለብን። ፍቅረ እግዚአብሔር እንዲኖረን/እንዲጨምር የሚያደርጉ ነገሮች :- እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ እንድትወደው ስለምትፈልገው ጉዳይ ከእርሱ ጋር ተነጋገር። የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ መጽሐፍ ቅዱስን እና ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎችን በማንበብ እግዚአብሔርን የበለጠ ማወቅ ትችላለህ። ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ያለህን ግንኙነት ያጠናክራል። በጸጥታ ጊዜ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ፍቅሩ ማሰብ በውስጥህ ያለውን ሰላም እና እምነት ያሳድጋል። በእግዚአብሔር ስራዎች ላይ ስታተኩር በህይወትህ ውስጥ እግዚአብሔር ያደረጋቸውን መልካም ነገሮች አስታውስ! ይህ ለእርሱ ያለህን ምስጋና፣የልቅ አቅርቦት እና ፍቅር ያሳድጋል። በጸሎት እና በትዕግስት እምነትህን ማሳደግ ትችላለህ። እነዚህ ነገሮችን በደምብ ስታስብ እና ስትተገብር ያኔ ከልብህ የሆነ ጸሎት፣ከልብ የሆነ እንባ፣ከልብ የሆነ እምነትን እያደረክ ትሄዳለህ ➤ ሁል ጊዜም ቢሆን ክርስቶስ ለኛ ያደረገልንን ነገር ማሰብ ነው ለአንተም ሲል ከሰማይ ወርዶ ሰው ሆኖ አንተን ከፍ ለማረግ እና ኃጢአትህን ይቅር ሊልህ መከራን ተቀብሎ ተስቅሎ ሞቶልሃል ይህን ፍቅሩን ሁልጊዜ ስታስብ ወደሱ ያቀርብሃል ➤ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ወይም አደርጉ ያለንን እየጠበቅህ፣እየሰራህ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው ለምሳሌ አስርቱ ትዕዛዛት፣የተራበን አብሉ የተጠሙትን አጠጡ...ያለንን፣አጽዋማት መጾም እና በዓላት ማክበር እነዚህ ነገሮችን ማድረግ ነው ጾም የሥጋ ፈቃዳችን ተገቶ የነፍስ ፈቃዳችን ስለሚበልጥ ነፍሳችን አብዝታ ወደ እግዚአብሔር ትቀርባለች፤በዓላትን ማክበር ደግሞ ለሱ ያለንን ፍቅር እና ምስጋና ምንገልጽበት ነው በረከቱም ለኛ ነው። ➤ ሌላው መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ስለ ንስሐ የተጻፉ መጽሐፎችን አንብብ ወደ እግዚአብሔር ይስብሃል ➤ መንፈሳዊ ፊልሞችን እይ ለምሳሌ አባ ሙሴ ጸሊም እና ግብጻዊቷ ማርያም እንዴት ከጨለማ ሕይወት ወጥተው ወደ እግዚአብሔር እንደቀረቡ ብርታት ይሰጥሃል.... ✅ከምንም በላይ ደግሞ ከንስሐ አባትህ ጋር ይሄንንም ሆነ ሌላ የሚያጋጥሙህን ችግሮች ተማከር/አማክር እንጂ በራስህ ሃሳብ ብቻ እንዳትስት በሰውም አስተያየት እንዳትስት የንስሐ አባት እያሉህ ሌላ አትፈልግ ከሳቸው ጋር ያለህ ግንኙነት ዝምብሎ ንስሐ ተቀብሎ ተፈቶ ለመሄድ እና ለመባረክ ብቻ ሳይሆን የሚገጥሙህን ማንኛውም ችግሮች እና መንፈሳዊ ነገሮች ጭምር እንድትወያይ ነው።
Oct 18, 2025