ለምን እግዚያብሔር ለምን በቃ ለምን 🥲 ለምን ብቸኛ እንድሆን ፈለገ? ለምን ጤና እንዳጣ ፈለገ? ለምን እናቴን እና እኔን ብቻ አስቀረ? ለምን እህት ወንድም የለኝም? ለምን የሚያግዝ ዘመድ አጣሁ? ለምን አባቴ አያቴ ሞቱ? ለምን እናቴ አንድ ወንድም ብቻ ኖራት? ለምን አባቴ እህት ወንድም የለውም? ለምን ጉደኛዬ የለኝም? ለምን ጉደኛዬ የነበሩት ወደሰው ሀገር እንዲሄዱ አደረክ? ለምትወደው ሰው ሰው አይደለም የምሰጠው ነው እኔን አትወደኝም? ለምን ብቻዬን ቀረሁ? ለምን አንገቴን ኦፕሬሽን ተሰራሁ? ለምን የካልሽየም እጥረት መጣ? ለምን ገንዘብ አጣሁ? ለምን ድጋሜ እንድሰራ ፈለክ? ለምን ጡቴን ተስራሁ? ለምን አሁን እባጭ መጣ? ለእናቴ እንዳልናገር ፈራሁ ለማን ልናገር እግዚአብሔር ሆይ ሁሉም አልጠይቅም ገንዘብ :ጤና :ሰው :.. እኔ ጤና መረጥሁ 🥲 እስኪ ያሳለፍኩን የሚያስጠላ ጊዜ አሁን ያለሁበትን ሁሉም የሚያስረሳ ነገር ነገሩኝ 🙏🏽
Oct 13, 2025ያልሸበትን የሚያስረሳ ነገር የእግዚአብሔር ቃል ነው። የዘረዘርሽው ጥያቄ እንኳን ቢመለስ ሌላ ነገር መፈለግሽ አይቀርም መቼም አይሞላም ሁሌ ይጎድላል. . . ይሄን የሚሞላው እንደኛ በነገር ሁሉ የተፈተነው የሰው ልጀ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። በእሱ በኩል እግዚአብሔር አብ የሰው ልጆችን ጥያቄ ሁሉ ሊመልስ ልጁን ሰው እንዲሆን ልኮታል። እግዚአብሔር አሁን ሰው ሆኗል። ያ ሰውም ያለኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም እያለ ሲናገር ሰምተነዋል። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል እያነበብሽ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አድርጊ መልሱ ይመጣል። እምነት በመስማት ነው ይላል። ያነበብሽውን የሰማሽውን አምነሽ ጠብቂው። እምነትሽ ነው የሚያሸንፈው አይዞሽ። 28፤እናንተ፡ደካማዎች፡ሸክማችኹ፡የከበደ፡ዅሉ፥ወደ፡እኔ፡ኑ፥እኔም፡አሳርፋችዃለኹ። 29፤ቀንበሬን፡በላያችኹ፡ተሸከሙ፡ከእኔም፡ተማሩ፥እኔ፡የዋህ፡በልቤም፡ትሑት፡ነኝና፥ለነፍሳችኹም፡ ዕረፍት፡ታገኛላችኹ፤ 30፤ቀንበሬ፡ልዝብ፡ሸክሜም፡ቀሊል፡ነውና።
Oct 13, 2025