በህልም የሞተን ሰው ደጋግሞ መመልከት 1, ሰውዬውን የምናየው በጥሩ ሁኔታ ከሆነ( ማለትም ፈገግ ብሎ ሲስቅ ሲጫወት ወ.ዘ.ተ) ይህ የሚያሳየው ሰውዬው ጥሩ የቀብር ሃያትን እያሳለፈ እንደሆነ ነው። 2, ሰውዬው የሞተው በቅርብ ጊዜ ከሆነ ድብቁ የአዕምሮአችን ክፍል (unconcious mind) ከሟቹ ጋር በሞት መለያየትን ገና አምኖ እንዳልተቀበለ እና ከመናፋፈቅ የመነጨ እንደሆነ ያሳያል 3, የሞተን ሰው በጣም በተደጋጋሚ ማየት ያ ሰው ከአንዳች በኛ ላይ ከሚገኝ መጥፎ ስራ እያስጠነቀቀን እና በመጥፎ ስራችን እየመጣ ያለን በላዕ እየተከላከለልን እንደሆነም ያሳያል ፤ ስለዚህ ይህ ነገር በተደጋጋሚ ሲገጥመን ወደ ራሳችን ማየትና ከባባድ አጥፊ ወንጀሎች ካሉብን እነሱን ማስወገድ ያሻል። 4, ሟቹ ከኛ ዱዐና ሰደቃ በተለይም ሰደቃን እንደሚፈልግ ማሳያም ይሆናል በመጨረሻም ቀብር ዚያራ ለሁለቱም ፆታዎች የተፈቀደ ነው ፤ የቀብር ዚያራ አደቦችን መጠበቅ ግን ወሳኝ ነው። ምናልባት የቀብሩ አስተዳዳሪዎች ከዚህ የተለየ አመለካከት ካላቸውም ለምን አይሆንም ብሎ ሰጣገባ አያስፈልግም ባለንበትም ሆነን ዱዐ ማድረግ ይቻላል። እና አብሽሪ እህታችን የሚያሳስብ ነገር የለውም
Oct 07, 2025