ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ? ዛሬ መስቀል አደባባይ ወይም saint Joseph ት/ት አካባቢ እኔ ወደ ሰፈር እየሄድሁ ከኔ በተቃራኒ አቅጣጫ አንድ ማየት የተሳነው ልጅ ወንድም ወደ የት ነህ ሸኘኝ አለኝ ከዛ ቆም ብዬ እኔ ወደተቃራኒ አቅጣጫ እንደሆንኩ ነግሬው የሚሸኝህ ሰው ላገናኝህ ስለው ጠጋ ብሎ መገናኛ ለመሄድ የታክሲ 20 ብር ጠየቀኝ እና የያዝሁትን ብር ሰጠሁት ብዙ አልያዝሁም ነበር። ከሸነሁት በኋላ ግን ለምን ከባንክ አውጥቼ አልሰጠሁትም፤ ችግሩንስ ለምን አልጠየቅሁትም የእራት ብር ባይኖረውስ ቤት ላይም ብር ባይኖረውስ፣ ሌላ የሚረዳው ባይኖርስ ብዬ ተጨነቅሁ እንዳጠፋሁ ተሰማኝ እና ደብሮኝ አመሸ አሁንም እንቅፍ አስቸገረኝ ምንም ሰላም አልሰማህ አለኝ። እናንተስ መረዳዳት ላይ እንዴት ናችሁ I know ኑሮ ለአብዛኛው ሰው በጣም ከባድ እንደሆነ። አጥፍቻለሁ እንዴ? ድጋሜ እንዴት ላገኘው እችላለሁ?
Oct 04, 2025This is humanity at its best, you did what is expected from you and don't overstressed bro
Oct 05, 2025