ሰላም ወዳጆቼ🙏 ይሄ ጆሮ ውስጥ አለ የሚባለው ትል ይሁን ነፍሳት ጆሮዬ ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል፣ ይሄን ዘበን ደሞ አንዳንዴ ትኝቼ ሳዳምጥ ሲንቀሳቀስ ሁሉ ይሰማኛል፣ የት እንደምሄድ እና ማንን እንደምጠይቅ ግራ ገባኝ፣ በማርያም እንደው መፍትሄ ካላቹ😌🙏
Oct 04, 2025ማንኛውም ከአንገት በላይ ህክምና (ENT) ያለበት ቦታ ቢሄዱ ይመራል ። ሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ውስጥ ባይኝም እንደ የካቲት አና ጥቁር አንበሳ ባሉ ተቋማት እንዲሁም እንደ ኦሲስ ባሉ የግል ስፔሻሊቲ ክሊኒኮች ኣገልግሎቱ ይሰጣል። የጆሮን የውስጥ ክፍል ማያ መሳሪያ (Otoscope) በመጠቀም ነፍሳት ወይም ሌላ ባዕድ ነገሮች ካሉ መመልከት ይቻላል ። አንዳንድ ጊዜ የጆሮ የውስጥ ክፍል ኢንፌክሽኝ (Otitis media) ተመሳሳይ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል ከዚህ ጋር ተያይዞ የጆሮ ማሳከክ፣ ፈሳሽ ማመንጨት እንዲሁም የድምጽ መቀነስ ሊኖር ይችላል። ለማንኛውም በቶሎ መታየት ያስፈልጋል።
Oct 04, 2025