ሰላም እባካቹ ስለ ስረዐተ ተክሊል ጋብቻ አስረዱኝ በተክሊል ለማግባት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጥልቀት አስረዱኝ እግዚአብሔር ያክብርልኝ
Oct 01, 2025https://t.me/Tewahdo_Haymanotie (እዚህ ቻናል ላይ "ተክሊል" ብለህ ሰርች አርግና በዛ ቃል የተቀመጡትን እያንዳንዱ ጽሑፎች ወደታችም ተከታይ ክፍል ያላቸውን እያየህ አንብብ ለዚህ ክብርና የተቀደሰ ጋብቻ ለመብቃትም የሚያስፈልጉ ነገሮች :- 1. የሃይማኖት አንድነት ወጣቶች በሃይማኖት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መሆን አለባቸው። 2. ድንግልና የተክሊል ሥርዓት የሚፈፀምላቸው ወጣቶች ራሳቸውን ከዝሙት ጠብቀው በድንግልና የፀኑ መሆን አለባቸው። 3. መፈቃቀድ የሚጋቡት ወጣቶች አንዳቸው ሌላውን ሊፈቅዱ ሊወዱ ያስፈልጋል።የሁለቱ መፈቃቀድ ሳይኖር በወላጆች ተፅእኖ ብቻ ሥርዓተ ተክሊል ጋብቻ ሊፈፀም አይችልም ። ለዚነው በሥርዓቱ ላይ አንደኛው ሌላውን «ወድጀ ፈቅጀ የምቀርበው»አንዳንድ ጊዜ ለምንድነው ወደ ቤተ-ክርስቲያን ተቀብያታለው ወይም ተቀብየዋለው ብለው ቃል የሚገቡት። 4. እድሜ የሚጋቡት ወጣቶች እድሚያቸው ትዳር የሚጠብቀውን ኃላፊነት ለመወጣት ብቁ ሊሆኑ ያስፈልጋል ለዚህም አስቀድሞ በፍትሀ ነገስት እንደተገለፀው ሴቷ 15ወንዱ ደግሞ 18አመት የሞላቸው መሆን አለባቸው ።እንደዚህም ሁኖ ሌሎች ነገሮች ካልተሟሉ ከዚህ በላይ ቢሆን መልካም ነው። 5. የንስሐ አባት ምስክርነት ሥርዓተ ተክሊል የሚፈፀምላቸው ወጣቶች አስቀድመው ንስሐ እየገቡ ንፅህናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የግድ የንስሐ አባት ሊይዝ ያስፈልጋል።ለንስሐ አባታቸውም ስለጋብቻቸውም ሆነ ስለ ማንኛውም ሕይወታቸው ሊያማክሩ ይገባል ። በዘመናችን አልፎ አልፎ እንደሚታየው «ገንዘብ ከፍየ ወይንም ደብረ ሊባኖስ ሂጀ አገባለው»እያሉ ተደብቆ ስርአተ ተክሊል መፈፀም አይቻልም። ተጋቢወች ካላይ የተጠቀሱትን ማሟላታቸውን በንስሀ አባት ሊረጋገጥና ይህም ሊመሰከርላቸው ያስፈልጋል። በመሆኑም የተጋቢወች መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ኑሮ በንስሀ አባታቸው ፊት የተገለጠ ሊሆን ይገባል። 6. የኑሮ/ኢኮኖሚ አቅማቸው ሁለቱም ተጋቢወች ወይንም ከሁለቱ አንዱ ወገን ራሱን የቻለ ሊሆን ያስፈልጋል ።የኢኮኖሚ አቅማቸውም ቤተሰቡን ለማስተዳደር በቂ መሆኑ ሊረጋገጥ ይገባል። 7. ስለ ትዳር ማወቅ (በቂ ግንዛቤ) ተጋቢወች ከመጋባታቸው በፊት ስለ ትዳርና አጠቃላይ ስለ ተክሊል ጋብቻ በሚገባ ሊያውቁ ይገባል።ትዳር በሦስተኛው ሰው ግፊት የሚፈፅምና ለጥቅማጥቅም ተብሎ ካልሆነም ለሙከራ የሚገባበት ሳይሆን ከልብ በመነጨ ፍቅርና ለትዳር ባለወ ግንዛቤ ስለትዳር በቂ እውቀት መኖር ግድ ይላል ስለተክሊም ቢሆን ከ አባቶችና በሰንበት ትምህር ቤት በቂ እውቀት ሊኖር ይገባል። እንግህ ተጋቢወች ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች ካሟሉ የተቀደሰውን የሥርዓተ ተክሊል ጋብቻ ሊፈፀምላቸው ይችላል።
Oct 01, 2025