✅33ቱ የእመቤታችን በዓላት የሚባሉት እነማን ናቸው? መቼ ይከበራሉ? የሚለውን በዝርዝር እንመለከታለን፡፡ 1.ነሐሴ 7- እመቤታችን ከአባቷ ቅዱስ እያቄምና እና ከእናቷ ቅድስት ሐና የተጸነሰችበት ቀን ነው፡፡ 2.ነሐሴ 16 – ሥጋዋ የፈለሰበት፤ ከሞት ተለይታ የተነሳችበትና ወደ ሰማይ ያረገችበት ቀን ነው፡፡ 3.ነሐሴ 17 – የእመቤታችን ትንሣዔ ይከበራል፡፡ 4.ነሐሴ 18 – የእመቤታችን ትንሣዔ ይከበራል፡፡ 5.ነሐሴ 19 – የእመቤታችን ትንሣዔ ይከበራል፡፡ 6.ነሐሴ 20 – የእመቤታችን ትንሣዔ ይከበራል፡፡ 7.ነሐሴ 21 – የእመቤታችን ትንሣዔ የሚከበርበት እንዲሁም ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓሏ ነው፡፡ 8.መስከረም 10 – ሥጋ የለበሰች የምትመስለውና ብዙ ተአምራትን የምታደርገው የእመቤታችን ስዕል ፄዴንያ በተባለ ቦታ ገብታ የተቀመጠችበት ዕለት ነው፡፡ 9.መስከረም 21 – ከሚያዝያ እስከ መስከረም 21 ቀን የተሰባሰቡት አባቶች በበ326 ዓ.ም አርዮስን ለማውገዝ ምልዓተ ጉባዔ የጀመሩበት ስለሆን የመስከረም ማርያም “የብዙኃን ማርያም” ትባላለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የክርስቶስን ቅዱስ መስቀል ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም ያስገቡበት ዕለት ስለሆነ በዓሉ በግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም በድምቀት ይከበራል፡፡ 10.ጥቅምት 21 – እመቤታችን በዚህ ቀን ትከብራለች፤ የግዝት በዓል ነው፡፡ 11.ኅዳር 6 – ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ ሀገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል ሀገር ገብታ ያረፈችበት ዕለት ነው፡፡ 12.ኅዳር 21 – የሙሴ ጽላት (ጽላተ ሙሴ) በአክሱም ቤተ መቅደስ በክብር የገባችበት እንዲሁም ካህኑ ዘካርያስ የእመቤታችን ምሳሌ የሆነውን የመቅረዝ ፋና ሲበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡ 13.ታኅሣሥ 3 – ከእናትና አባቷ ተለይታ በ3 ዓመቷ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው፡፡ 14.ታኅሣሥ 21 – በዚህም ዕለት እመቤታችን ትከብራለች፡፡ 15.ታኅሣሥ 22 – ቅዱስ ደቅስዮስ እመቤታችን ጌታን የጸነሰችበትን የመጋቢት 29 ቀንን በዚህ ዕለት አከበረ፡፡ 16.ታኅሣሥ 29 – ጌታችንን የወለደችበት ዕለት ነው፡፡ 17– ጌታችንን የወለደችበት ዕለት ነው፡፡ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ወርሃ ጳጉሜን ስድስት ቀን ስትሆን ልደት በ28 ይውላል፡፡ 18.ጥር 21 – በ64 ዓመቷ ያረፈችበት ዕለት ነው፡፡ 19.የካቲት 16 – እመቤታችን ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ ቃል ኪዳንን የተቀበለችበት ዕለት ነው፡፡ 20.የካቲት 21 – ወርሃዊ የግዝት በዓሏ ነው፡፡ 21.መጋቢት 21 – በዚህ ዕለት እመቤታች ትከብራለች፡፡ 22.ማጋቢት 29 – ጌታችንን የጸነሰችበት ጥንተ በዓል ነው፡፡ 23.ሚያዝያ 21 – የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡ 24.ግንቦት 1 – ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችበት ዕለት ነው፡፡ 25.ግንቦት 21 – በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት ዕለት ነው፡፡ 26.ግንቦት 22 – በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡ 27.ግንቦት 23 – በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡ 28.ግንቦት 24 – ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ ሀገር የገባችበት ዕለት ነው፡፡ 29.ግንቦት 25 – ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት ነው፡፡ 30.ሰኔ 8 – ተወዳጅ ልጇ ከደረቅ ዓለት ላይ ውኃ ያፈለቀበት ነው፡፡ 31.ሰኔ 20- ጌታችን ተገልጦ ሐዋርያቱን ሰብስቦ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ያሰራበት ዕለት ነው፡፡ 32.ሰኔ 21 – ቅዳሴ ቤቷን ያከበረበት ዕለት ነው፡፡ 33.ሐምሌ 21 – በዚህ ዕለትም የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡ 🙏የእመቤታችን ጣዕሟን በአንደበታችን ፍቅሯን በልባችን ታሰድርብን የልጇ የክርስቶስ ቸርነት አይለየን፡፡🤲
Sep 29, 2025