#religion Scripture clearly affirms Christ as the sole mediator between God and mankind (John 14:6, 1 Timothy 2:5). Within Orthodox practice, however, we faithfully honor the Theotokos ( Marry) and ask for her intercessions. This creates a point of confusion for me: how do we properly understand her role as an intercessor without compromising the biblical teaching of Christ’s UNIQUE mediatorship? How have the Church Fathers explained this relationship between Christ’s exclusive mediation and the intercessory prayers of the saints? Ultimately, how should we as Orthodox Christians hold both truths together: firmly believing in Christ as the one Mediator while also faithfully seeking the prayers of the Theotokos(Saint Marry) and the saints? By: Anonymous Status: Previewing
Sep 20, 2025" ስለ እኛ የሚማልደው ....." 👉 " ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ " ምን ማለት ነው? 👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሮሜ 8፥34ን ምን ብሎ ተረጎመው 👉 "መካከለኛ" የተባለበት ምክኒያት 👉 #የቅዱሳን_አማላጅነት_ትምህርት_የኢየሱስ_ክርስቶስን_መካከለኛነት_ይቃወማል/ይጋፋል_? +++++++++++++~~~++++++++++ ታዲያ እንዲህ ከአብ ጋር በከሃሊነትና በሥልጣን አንድ የሆነ እርሱ እኛን ለመርዳት ማላጅ መሆን እንዴት ያስፈልገዋል? እንዴት እርሱ አማላጅ ይሆናል? እንዴት ይማልዳል ይባላል? የተፈረደባቸውንና የተኮነኑትን ነጻ ያወጣቸውና ያዳናቸው እርሱ፣ ከሞት ፍርድና ከኩነኔ ነጻ ያወጣና ያዳነ እርሱ፣ ጻድቃንና ልጆች ያደረጋቸው እና እጅግ ከፍ ወዳለ ክብር ያወጣቸው እርሱ፣ ይህን ሁሉ ከፈጸመና ካከናወነ በኋላ፣ ባሕርያችንን በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ካስቀመጠው በኋላ፣ በጣም ቀላል ስለሆኑት ነገሮች ማላጅ መሆን እንዴት ያስፈልገዋል? ሲዖልን በሥልጣኑ የበዘበዘ፣ ሞትን በኃይሉ የሻረ፣ ልጅነትንና ትንሣኤን የሰጠ፣ ባሕርያችንን ከራሱ ባሕርይ ጋር አዋሕዶ በሰማያት በንጉሡ ዙፋን ላይ ያስቀመጠው እርሱ፣ ስለ ጥቃቅን ነገሮች ለምን ለማኝ ማላጅ ይሆናል? (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ትርጓሜ መልእክተ ሮሜ) #መድሎተ_ጽድቅ #ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
Sep 20, 2025