ሰላም ለናንተ ቤተሰብ ፍቅረኛ አለችኝ እና የድሮ ታሪኳ ስሰማ ከብዙ ወንዶች ጋር እንደወጣች አረጋገጥሁ ከዛ አስጠላችኝ በዚህ መካከል ከሌላ ልጅ ጋር ማውራት ጀመርሁ እና ከሁለተኛዋ የበለጠ ፍቅር ያዘኝ ማግባት ምፈልገውም ሁለተኛዋን ነው። የመጀመሪያዋ ስራ አላት ሁለተኛዋ ግን ገና ተመርቃለች እኔ የሆነ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ ጥሩ የሚባል ገቢ አለኝ። ጥያቄዬ ምን መሰላችሁ የመጀመሪዋ ልጅ ከተውከኝ እራሴን አጠፋለሁ እያለች ስንጣላ እራሱ ፌንት እየበላች ነው ስለዚህ ሳልጎዳት እንዴት ልለያት ከሷ ለመለየት ብዙ ሞክሬ አልተሳካልኝም። የመጀመሪያዋ ጋር ፍቅር ስንጀምር ጨዋ እንደሆነች ትነግረኝ ነበር ግን አልነበረችም። ከሁለተኛዋ ጋር ልንጋባ ተስማምተናል። ሳትፈርዱ ምክር ስጡኝ
Sep 18, 2025በአሁን ሰአት የምትወድህ ሴት ተገንቶ ነው? ወይስ እጅህ ላይ ስትሆን ቀለለችብህ? ያለፈው እኮ ፓስት ነው። አሁን ፕረዘንት ላይ ነህ። የመጀመሪያዋ ክብር ፍቅር የምትሰጥህ ሴት ከሆነች አግባት አንተም ውደዳት። ግን ስገምት አስጠላችኝ አልክ። ብታገባትም ፓስት ኤክስፕሪያንሷን እያነሳህ ልትጎዳት ነው። እንደኔ እንደኔ ንግግርህ ለራሱ ህፃንነትህን ያሳያል። አልበሰልክም ወንድሜ። እንደኔ እንደኔ ትዳር ውስጥ አትግባ ገና ያልገቡህ ነገሮች አሉ። ሲገባህ ትረስትሚ የመጀመሪያዋ ከማንም ሴት በላይ ምርጥ ሴት እንደሆነች መረዳት ትጀምራለህ። ጭራሽ ደበረችኝ? ስንት ባለጌ ወንድ ያለበት ዘመን እኮ ነው። ኤክስ ጋር ወሲብ ማድረግ ኖርማል ነው። ብሮ አታካብድ! ሁሉም አስመሳይ ሆኖ እንጂ አንተም በሌላ ሴት እንዲህ የምትባልበት ኤክስፕሪያንስ ሊኖርህ ይችላል።
Sep 18, 2025