የቀጠለ 2ተኛ ሀሳብ 2, ምንም ምንም በሚባል ደረጃ አላነበብኩም ወላሂ። ገና ከ 10ኛ ክፍል ነው ተስፋ ቆርጬ ሀሳቤ ሌላ የነበረው። በቃ ክላስ ገብቼ አላውቅ ፅፌ አላውቅ ግን english ሰቅዬው ሌሎቹም ትንሽ ከፍ ብለው አለፍኩ። 2 ስሜት ነው የተሰማኝ የደስታም ግር የማለትም cause ምማርበት ቦታ እያደሩ ሚያነቡ፣አንጥፈው እየተኙ ሚያነቡ ነበሩ እና they failed። ማይገባኝን ስለያዝኩ በቃ ለነሱ ቢሰጣቸው ደስተኛ ነኝ። እኔ remedial ቢመጣም ምንም አይመስለኝም ነበር። እና ከምር ህይወት ደስተኛ ሁኜ ስታስጠላኝ የመጀመሪያዬ ነው። is this feeling normal? 3: ህይወቴ ትምህርት ላይ depend የሆነ ነው? የተለያዩ ነገሮችን even forex እየተማርኩ ነበር። ግን አሁን ሲመጣ ብዙ ሰው including ዘመድ የራሱን ሀሳብ እየሰጠ familyንም እኔንም spoil እያረገ ተጨነኩ። ያለ ትምህርት የትም አትደርስም ማለት ነው የቀራቸው። እኔ ሀሳቤ አለመማር አይደለም ግን ተረጋግቼ የራስ ነገር ኑሮኝ እየሰራውም ብማር አይጎዳም ብዬ ነው ማስበው። የቀን ካልሆነ ደግሞ ብሎ ብዙ ሰው ሙጭጭ ብሏል። የምር ግራ ገብቶኛል😭 ተምሬ 9 to 5 job ነው ሚታየኝ እኔ ደግሞ። የሰው ወሬ ሲበዛ የምር ይመስላል እና የምራቸውን ነው? እስኪ ሀሳባቹን ስጡኝ።
አሰላሙአለይኩም ፣ እስኪ ቢበዛም ሰብሰብ ብላቹ አንብቡ እና ሀሳባቹን ስጡኝ🤗። ዘንድሮ 12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ነበርኩ እና በማላውቀው ሁኔታ አለፍኩ🤷♂። አሁን ያለኝ 3 ሀሳብ ስሙኝ እና ሀሳባቹን ስጡኝ። 1, አልማርም ብዬ የተለያዩ ነገሮችን እየሞከርኩ ፋሚሊም ምወድቅ መስሏቸው በቃ ፊታችንን ከትምህርት አዙረን ነበር።እኔ አሁንም ሀሳቤን አልቀየርኩም ቋሚ የቀን አልማርም ግን ታላቅ እህቴ apply አርገህ የደረሰህ ሂድ አለቺኝ። "አሁን እንደዚህ ተማሪ እየወደቀ ስለሆነ after 5 years ብዙ ስራ እድል ይኖራል ስለዚህ መማር አለብህ ብላ ደረቀች። እኔ ደግሞ 5 አመት ምናምን እንደቀልድ ማቃጠል አልፈልግም እየሰራው መማር እንጂ። በዛውም ከተማ፣ሰዎችን እና ህይወትን ማወቅ ይሆነኛል ብዬ ነው ማስበው። እሷ ግን በቃ ትማራለህ ላይ ነች። እኔ ደሞ በቋሚ አላረገውም ብያለው። በዛ ላይ my families are poor። ሂጄ እሷንም መጠየቅ አልፈልግም ጎደለብኝ ብዬ። የማን ሀሳብ የተሻለ ነው? 2 እና 3 በሌላ እመለሳለው ስለሚበዛ። ሀሳባቹን ስጡ