"ቀጣዩ ትውልድ በደንብ የሚያስፈልገዉ ክህሎት እንዴት መማር እንዳለበትን መማር ነው"- ደሚስ ሃሳቢስ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ላይ የሚሰራው የጎግሉ ዲፕማይንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ደሚስ ሃሳቢስ ቀጣዩ ትውልድ የሚያስፈልገው ትልቁ ክህሎት እንዴት መማር እንዳለበት መማር ነው ብለዋል። ስራ አስፈፃሚው ይህ ክህሎት ያስፈለገው የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሰዎች የሚማሩበትና የሚሰሩበትን መንገድ እየቀየረ በመሆኑ ስለመሆኑ ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውህሎት በየሳምንቱ እየተቀያየረ መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ከ10 ዓመት በኋላ የሚሆነውን መገመት ከባድ መሆኑን ተናግረው በጣም ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ነው ሲሉ ነው የገለጹት። በ2024 በኬሚስትሪ የኖቤል ሽልማትን ያሸነፉት ደሚስ ሃሳቢስ እንደ የሰው ልጅ የበሰሉ ወይም የሰው ልጅ ማከናወን የሚችለውን ነገር በብዛት መስራት የሚችል የሰው ሰራሽ አስተውህሎት በ10 አመት ውስጥ እንደሚመጣ አንስተው ሰዎች እንዴት መማር እንዳለባቸውና ከተለመዱት ትምህርቶች ውጪ ራሳቸውን ለአዲስ ነገር ማዘጋጀት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ከመጣ ወዲህ ዓለማችንን በእጅጉ እየቀየረ ሲሆን መጥፎም ጥሩ ጎኖችንም ይዞ ብቅ ብሏል። የትምህርት ዘርፉን ጨምሮ በርከት ያሉ ዘርፎች ከቴክኖሎጂው መምጣት በኋላ ሲቀየሩ ተማሪዎች በቴክኖሎጂው ላይ ይበልጥ ጥገኛ መሆናቸው የማሰብ ችሎታቸውን እንደሚያዳክም ይነገራል። አንዳንድ ስራዎችም በሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያዎች እየተተኩ ሲሆን ዘርፉ ግን ስራን ከመተካት በተጨማሪ በርከት ያሉ ሌሎች ስራዎችን እንደሚፈጥር የሚሟገቱ አሉ። የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ምድርን እየለወጠ ባለበት ሁኔታ ነገሩን እንዴት መያዝ አለብን የሚለው ትልቅ ጥያቄ ሲሆን እንደ ሃገር ከዘርፉ መጠቀም እንድንችል ምርምር እና ትምህርቶችም ያስፈልጋሉ። መረጃው የMINT ነው። @TikvahethMagazine
Sep 16, 2025