ሰላም ቤተሰብ እህቴ ዛሬ ጠዋት ከመሬት ተነስታ አጠገቤ ቆመችና "እኔ ግን ላንተ ክፉ ሰው ነኝ?" አለችኝ። በጣም ከፍቷት ነበር። እያለቀሰች ቀጥላ እንዲ አለችኝ ለምን እንደሱ አልሽ ስላት... ሰው ሁሉ ይጠላኛል ለምንድነው ግን አለች። ምን እንደምላት ስላላወኩ ላጽናናት አልቻልኩም። ቤተሰቦቻችን በፍቅር አላሳደጉንም። እናትና አባታችን ልጅ እያለን ነው የተለያዩት። ያሳደገችን እናታችናት እና ፍቅር መገላለጽ አንችልም። ምንም አንዳችን ላንዳችን ፍቅር ቢኖረንም ግን ያንን በቃል መገላለጽ አለመድንም። እኔኮ እወድሻለሁ እህቴ ክፉሽን ራሱ ማይበት አቅም የለኝም ልላት ፈልጌ እንዴት ላውጣው። እባካችሁን ከዚ ስሜት እኝድቶጣ የሆነ ነገር ጻፉላት። እኔ ምን እንደምላት ግራ ገብቶኛል እባካችሁን። እባካችሁን እህቴን እርዱልኝ። 😔
Sep 15, 2025እንደምትወዳት እና ነብስህን አሳልፈህ እስከመስጠት እንደምትወዳት ለሰከንድ እንዲከፋት እንደማትፈልግ ንገራት ብቸኝነት መጥፎ ነው የአለመፈለግ ስሜትን አቀዋለሁ በጣም ተስፋ ያስቆርጣል ሞት ያስመኝሀል ብቻ እንዳታጣት ካሁኑ እሷ ላንተ ምን ማለት እንደሆነች ንገራት ከረፈደ በኋላ ከመቆጨት አሁን ድረስላት አብረሀት ጊዜ አሳልፍ pls brother
Sep 15, 2025