የኑሮ ዉድነቱን, በዘር በሀይማኖት መከፋፈሉን ለማስቀረት የዚህ መንግስት መዉረድ ብቻ በቂ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ወይስ ሌላ መንገድ አለ
Sep 10, 2025እንዲህ አይነት ጥያቄ ውስጥ ጭፍን የሆነን ጥላቻ እመለከታለሁ። ይህን በጭፍን ጥላቻ የተሸፈነ ጥያቄ ለመመለስ መመልከት ያሉብን ነጥቦችን በጥያቄና መልስ መልኩ ላንሳ። ዋና ነጥቦች - የኑሮ ውድነት - በዘርና ሀይማኖት መከፋፈል - የዚህ መንግስት መውረድ/መቀጠል የኑሮ ውድነት እንደ አገር ያለንበት የኑሮ ውድነት (Inflation) የተከሰተው በኛ አገር ብቻ ነው? ወይስ በሌሎች አገራትም ተከስቷል? አሁን ያለንበት የኑሮ ውድነት የተከሰተው በዚህ መንግስት ነው? ወይስ ባለፉ መንግስታትም የነበረ ነገር ነው? መልስ እንደ አገር ያለንበት የኑሮ ውድነት (Inflation) የተከሰተው በኛ አገር ብቻ ነው ወይስ በሌሎች አገራትም ተከስቷል ለሚለው ጥያቄ.. ሁለት ዕይታዎችን መያዝ ይኖርብናል። አንደኛው መንግስት ከቁጥጥሩ ውጭ በሆኑ ፋክተሮች የተነሳ የሸቀጦች ዋጋ መናር ይከሰታል። ባለንበት ተጨባጭ ኮሮና፣ የአገር ውስጥ ግጭቶች/ጦርነቶች፣ የውጭ አገራት ጦርነቶች (ሩሲያና ዩክሬን፣ ፍልስጤምና እስራኤል) እና ይህን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ (Since most of the countries that are in current conflict are petroleum providers)፣ የአሜሪካ-ሩሲያና ቻይና ፍጥጫ እና አንዳቸው በአንዳቸው ላይ የሚጥሉት የታሪፍ ጭማሪ እና ይህን ተከትሎ በሸቀጦች ላይ የሚፈጠረው የዋጋ መናር፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የሰራተኞች ቁጥር ካለው የህዝብ ቁጥር ምጥጥን አለመኖር (አንድ የሚሰራ አባወራ ምናልባት ለሁለትና ከዚያ በላይ የማይሰሩ ሰዎች ሰርቶ ማስተዳደር ይኖርበታል። ይህም ጫናውን ከፍ ያደርገዋል)... እነዚህ ሁሉ የጠቀስኳቸውና ያልጠቀስኳቸው ነገሮች ተደማምረው መንግስት ሳይፈልግ + ኅብረተሰቡ ሸቀጦች ላይ ዋጋ ይጨምራል። ሌላ * መንግስት ኢንቨስተሮችን ለማበረታታት ፈልጎ የአገራችንን ገንዘብ (ብር) የመግዛት አቅሙን ሆን ብሎ ያወርዳል። ሌላ * ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ሲል የገንዘቡን የመግዛት አቅም ሊያዳክመው ይችላል። ሌላ * ወጪን ለማበረታታት (የገንዘብ አቅም የሚጨምር ከሆነ በገንዘቡ ከመስራት ይልቅ መያዝን ይመርጣል። ገንዘቡ አቅሙ ሲዳከም ከመያዝ ይልቅ ይሰራበታል።) ስለዚህ ጠቅለል ስናደርገው መንግስት ፈልጎም ተገዶም የዋጋ ንረት በአገሪቱ ሊከሰትበት ይችላል። ጥያቄውን ስመልስልህ.. የኑሮ ውድነቱ ቅድም በተጠቀሱ ፋክተሮች ምክንያት መጠኑ ይለያይ እንጂ በሁሉም የአለም አገራት ላይ መከሰቱ አይቀርም። በዋጋ ንረት ኢትዮጵያ በ31.4% በአለማችን 11ኛ ላይ ትገኛለች። 1. ቬንዙዌላ 400% 2. ዚምባቡዌ 172% 3. አርጀንቲና 98.6% 5. ቱርክ 50.6% 9. ኢራን 42.5% 16. ግብጽ 21.6% 17. ዩክሬይን 21.1% 18. ናይጄሪያ 20.1% ስለዚህ እንደውም በሰውየው ጉብዝና ሆኖ እንጂ ከዚህ በኩል እንደ አባይ ያለን ግዙፍ ፕሮጀክት ይዘን፣ ሌሎች ግዙፍ ፖሮጀክቶች ኖረው፣ ጦርነቱ፣ ሙስናው፣ የወጣቱ ስንፍና... ተደራርበው ቬንዙዌላን የሚያስንቅ ግሽበት ሊጠብቀን ይገባ ነበር። በዚሁ በኑሮ ውድነት የተነሳው ጥያቄ.. አሁን ያለንበት የኑሮ ውድነት የተከሰተው በዚህ መንግስት ነው? ወይስ ባለፉ መንግስታትም የነበረ ነገር ነው የሚለው ነው። አጭር መልሱ: በዚህ መንግስት ብቻ የተከሰተ ነገር አይደለም። በመለስ ዘመን (1999) ሳሙና ከ2ብር ተነስቶ 2 ብር ከ75 ሳንቲም ገባ ብለን ያማረርን ህዝቦች ነን (ቪድዮ አለኝ። ከመልሱ በኋላ እለቀዋለሁ)። ከላይ እንደጻፍኩት ነው። መጠኑ ይለያይ እንጂ የኑሮ ውድነቱ በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ መኖሩ አይቀሬ ነው። ስለዚህ መንግስት ቢቀየር አለመረጋጋት ተጨምሮበት ነገሮች ቢያሻቅቡ እንጂ መረጋጋት የሚባል ነገር አይታሰብም! የዛሬ ነጋዴ ደግሞ ራሱን ብልጥ ሌላውን ሞኝ አድርጎ የሚያስብበት ዘመን ነው። የሚብስ እንጂ የሚስተካከል ነገር አይጠበቅም። ሁለተኛ ነጥብ በዘርና ሀይማኖት መከፋፈል የጀመረው ይህ መንግስት ነው? አሁንም አይደለም። አብይ ባልጀመረው ነገር ጥፋተኛ አድርገነው እርሱ ቢወርድ "ይስተካከላል" ብለን ማሰባችን የዋህነት ነው። ዘረኝነት እንደ አዝርዕት ነው። አሁን ከተከልከው ጊዜ ጠብቆ ከትውልድ በኋላ ነው የሚያፈራው። በንጉሱ ዘመን የአንድ ብሔር እና ሀይማኖት የበላይነት ኖሮ "ንጉስ አይከሰስ፣ ሰማይ አይታረስ" በሚል ብሂል ሁሉም ፈርቶ ቅያሜውን በሆዱ ይዞ ኋላ 1966 ላይ ቅያሜው ፈንድቶ ንጉሱን 3 ሜትር የጠለቀ ቀብር አወረዳቸው። መንግስቱ ኃይለማርያም ደግሞ ወታደራዊ አገዛዝ ስለነበር የሚከተለው ሁሉም ዘርና እምነት እኩል ነበር። በአውራጃ ከፋፍሎ ነበር የሚገዛን። ለዘረኝነትና ሀይማኖት መከፋፈል እንዳይመች አድርጎ መርቶ ወረደ። ወደ ኢህአዴግ (ዘመነ-መለስ) ስንመጣ ለራሱ እነሰዲመቸው ፈልጎ የዘር ፖለቲካን ተከተለ። በብሔር ክልል መሠረተ። የኔነት በዛ። አንድ ጨቅላ ተወልዶ ለአቅመ አስተዋይነት እስኪደርስ ድረሰ (27 አመታት) ዘረኝነቱን ዘርቶ አበቀለብን። ፍሬውን በዘመነ-አብይ መመገብ ጀመርን። ስለዚህ ዘረኛው የመለሱ አገዛዝ የፈጠረው ቀውስ ነው ዛሬ ላለንበት ያበቃን። ይህን ለማስወገድ መፍትሔው የአብይ ከስልጣን መነሳት ማለት ለጉንፋን በሽታ የወባ መድሀኒት መስጠት ነው።
Sep 10, 2025