መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ መሰላቸት ፣ መነሳሳት ማጣት ፣ አይገባኝም ብሎ ማሰብ ፣ ባንድ ግዜ ሁሉም ነገር ካልገባኝ የሚል አስቸጋሪ መንፈስ ፣ ትግስት ማጣት በዛላይ ... በንደዚህና በመሰል ምክንያቶች ለምንቸገር በፊት በንደዚ ከይነት መንፈስ ምትቸገሩ አሁን ግን በጣም በጥሩ ሁኔታ እያነበባችሁ ያላችሁ እስቲ ልምዳቹን አካፍሉኝ። ከቻላቹ በ ቮይስ ካልቻላቹም አብራርታቹ ንገሩኝ የናንተን ልምድ። አመሰግናለሁ።
Sep 06, 2025ስንጀማምር ሁላችንም ሚገጥመን ነው ነገር ግን ከበረታህ በነዚህ መንገዶች የአንተም ሁኔታ ይስተካከላል ከምንም በላይ ደሞ ጸሎት እና አስቀድሞ መማር(ከመምህራንም መጠየቅ ነው) መጀመርያ በጸሎት ጀምር ለመሰላቸቱ ጊዜ እና ምዕራፍ መድበህ አንብብ ለምሳሌ በቀን 5 ምዕራፍ ለመነሳሳት ማጣት መጀመርያ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነት፣ዓላማ፣ጥቅም እና ሌሎች ነገሮችን ተማር ወይም አንብብ ከዛ እንድጀምረው ያነሳሳሃል ለአይገባኝም ብሎ ማሰቡ ከጸሎት ጋር ሆነህ በራስህ ለመፍታት ሳይሆን ከአንድምታ ትርጓሜዎች ጋር አንብብ በአንዴ ካልገባኝ ለሚለው ነገር ደግሞ በአንድምታ መጽሐፍት እና የበለጠ ከመምህራን ጠይቀህ መንፈስቅዱስም በጸሎት እየጠየክ እንጂ በራስህ ብቻ እንደማይሆን ራስህን አሳምን ለትእግስት ማጣቱ ከላይ እንዳልኩህ ቀኑን ሙሉ እዛ ላይ መዋል ሳይሆን በቀን ከ1 ምዕራፍ ጀምረህ ቀስ እያልክ ትጨምራለህ(ከአጠገብህ የሚረብሹ ነገሮችን አስወግድ)
Sep 06, 2025