እንዴት ናችሁ ባለፈው ሁላችሁም ተረጋጋ ምንም ማድረግ አትችልም ብላችሁኝ እኔም ሁሉንም ለመተው ሞክሬ ነበር ግን አልሆነም ሰሞኑን አሞኝ ነበር በዚሁ ምክንያት በቃ ወደ ቤት ስሄድ ካየኋቸው በጣም ልቤን ያመኛል ቤት ተከራይቼ ለመውጣት ደግሞ ከበደኝ በገንዘብ ምናምን ሳይሆን... በቃ ምንም አይመስሉኝም ልክ እንደማላቃቸው ሰው መሆን ጀመርኩ ከብዶኛል የሆነ ከልቤ ውስጥ የወጣ ነገር አለ ይቅርታ ላረግ አልቻልኩም እኔ ለነሱ ምን ያክል ርቀት እንደምሄድ ፈጣሪ ያቃል
ሰላም ለቤት የመጨረሻ ልጅ ነኝ እና በብዙ ችግር ውስጥ ነው የተማርኩት አባቴ ልጅ እያለሁ ነው ያረፈው ቤት ያለሁት ወንድ እኔ ብቻ ነኝ ያው ሁሉም ነገር አልፎ ተመርቄ ጥሩ የሚባል ስራ እየሰራሁ ቤተሰብንም ባለኝ አቅም እያገዝኩ ነው ከዛ ምን አይነት ችግር ተፈጠረ እኔ ምንም በማላቅበት ሁኔታ ትልቅ እህቴ ልታገባ እንደሆነ ሽማግሌ ሳይላክ ምናምን ቀን እንደተቆረጠ ነገሩኝ ያው እኔም ተናድጄም ቢሆን የሰርጉን ሙሉ ወጭ ሸፈንኩ የሰርጉ ቀን ራሱ አልተገኘሁም ነበር ትንሽ ወር ቆይተው ተፋቱ ይህንንም ቆይተው ነገሩኝ በዚህ ተናድጄ ሳላበቃ ጭራሽ እርጉዝ ሁናለች በቃ ምን ልበላችሁ ቤት ለማደር ብቻ ነው የምሄደው እነሱ ጋ ንግግር ካቆምኩ ቆየሁ ልቤ በጣም ተሰብሯል ጭራሽ ሰሞኑን ሳስብ ሁላ እያመመኝ ነው ምን ላርግ