እግሬን በጣም ያልበኛል አሁን ታጥቤው ትንሽ ቆይቶ ያልበኛል ከዛ ሽታ ያመጣል እማጠፋበት መንገድ ካለ እባካችሁ ንገሩኝ 🙏
Sep 03, 2025የእግር ሽታ የሚከሰተው ላብ ከባክቴሪያዎች ጋር በሚቀላቀልበት ጊዜ ነው። እግር ለምን ይሸታል? - ላብ + ባክቴሪያ = መጥፎ ሽታ - የፈንገስ ኢንፌክሽኖች - ካልሲ በጣም ለረጅም ጊዜ መልበስ ወይም ማድረግ - ደካማ የዓየር ፍሰት (አየር የማያስገቡ ጫማዎች) ለእግር ሽታ ፈጣን መፍትኄዎች! 1.በየቀኑ በፀረ-ባክቴሪያ ሳሙና መታጠብ እና እግርን በደንብ ማድረቅ! 2.በሚከተሉት ውህዶች እግርን መንከር ወይም መዘፍዘፍ፤ -ጥቁር ሻይ (black tea) (የቆዳ ቀዳዳዎችን ያጠባል) -ኢፕሰም ጨው (Epsom salt) + ኮምጣጤ (vinegar) (ባክቴሪያዎችን ይገድላል)። -ቤኪንግ ሶዳ (baking soda):- (እግር ሽታ እንዳይኖረው ያደርጋል)። 3.የእግር ዱቄት (foot powder) (ታልከም ወይም ሜዲኬትድ) ወይም አንቲፐርስፔራንት (antiperspirant) ስፕሬይ ይጠቀሙ። 4.ላብን እና እርጥበትን የሚመጡ ካልሲዎችን (ጥጥ/ባመቡ) ይልበሱ እንዲሁም ጫማ ይቀያይሩ። 5.ጫማዎትን ስፕሬይ በመርጨት ወይም ቻርኮል በመክተት ያጽዱ። የእግር ሽታ የማይጠፋ ከሆነ የሚከተሉት መድኃኒቶች በሐኪም ትዕዛዝ ይጠቀሙ -በሐኪም ማዘዣ የታዘዙ ጠንካራ አንቲፐርስፔራንት (antiperspirants) መድኃኒቶች። -ፀረ-ፈንገስ መድኃኒቶች (ለአስቸጋሪ ኢንፌክሽኖች) -ቦቶክስ (Botox) (ለከፍተኛ ላብ)። እነዚህን መድኃኒቶች በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ መጠቅም ያስፈልጋል!! የመከላከያ ምክሮች -እግርዎ ዓየር እንዲያገኝ ቤት ውስጥ ሲሆኑ በቦዶ እግርዎ ይሂዱ። -ባክቴሪያዎችን ለማጥፋት በፀሐይ የደረቁ ጫማዎችን ያድርጉ። - እግርዎን በጣም ካላብዎት እኩለ ቀን ላይ ካልሲ ይቀይሩ።
Sep 03, 2025