ሰላም ሁላችሁም እንዴት ናችሁ አሁን ላይ እያስጨነቀኝ ያለ ጉዳይ አለ 🥺ውሳኔ ላይ መድረስ ስላቃተኝ የናነተን ሀሳብ ፈልጌ ነው:: ከሁለት ወር በፊት አንድ ስራ ተቀጠርኩ ከሌላ አንዲት ልጅ ጋር ስለ ስራው እውቀቱና ልምዱ ባይኖረኝም በዝቅተኛ ደሞዝ ለልምዱ በዛም ላይ ሌላ አማራጭ ስለሌለኝ ስራውን ጀመርኩ አብራኝ የተቀጠረችውም ልጅ ልምድ የላትም ቢሮ ውስጥ አንድ የቢሮ ሀላፊ አለ ሁሉንም ነገር ያሳያችኋል ያሉንም እሱን ነው ግን ከቅርብ ቀናት ወዲህ በተለይ ከኔ ጋር የግል ፀብ እንዳለዉ ሰው ነው act እያረገብኝ ያለው ስራ ላይ ስህተት ከሰራሁማ በቃ እንዴት እንደሚናገረኝ የአለቃ ፀባይ ነው ብዬ እንዳላስብ እኔላይ ሲሆን በቃ the way he talk erasu yelayal. After this all disrespect& undermining he showed to me በቃ የማረገው ግራ ገባኝእኮ በማሪያም ስራውን እንዳልተው እንዴት ቢያንስ ትምህርቴን cover እንኳን የማረግበት አማራጭ የለኝ ልቀጥል ስል ደሞ ቀን በቀን በእንደዚህ አይነት environment ውስጥ እንዴት እባካችሁ ሃሳባችሁ ያስፈልገኛል በጣም ጭንቅላቴ ማሰብ ከሚችለው በላይ ስለሆነብኝ ነው😓😓😓
Aug 30, 2025ሁሉም ቦታ ነው። አንተን ጥፋተኛ ለማድረግ እና ወንጀለኛ እድትሆን ራሳቸው የማይሰሩትን ነገር እንድትሰራ የሚያረጉ አለቃዎች አሉ በየእለቱ ከድርጅቱ እንድትወጣ ቀን በቀን ጉድጓድ የሚቆፍሩልህ ምንም ኮ አላደረካቸውም። እንደነሱም ክፉ ለመሆን እና ስልጣንን ለመቆናጠጥ ሀብት ለማካበት እንዳታስብ በተቻለ አቅም በእየ እለቱ በፈተኑህ ቁጥር አንተ መሆን ያለብህ ሰው ለማድረግ ብቻ እንደሆነ ተረዳ!! ህመም ሰተውን ቆሻሻችንን የሚያጥቡልን ስንቶች ናቸው። በተለይ አንተ መስሪያ ቤቱን ለመልቀቅ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ካለህ ማድረግ ያለብህ ራስህን ማረጋጋት ነው። እና ራስህን ማስከበርም ይኖርብሃል ። ስራ ትሰራለህ ከተሳሳትክ ሰው ነህ አንተ ፍፁም አይደለህም ሰው ነኝ እሳሳታለሁ በለው ከዛ በላይ ትኩረት ራሱ እንዳትሰጠው እና አለቆች እንደዚህ መሆን ባህሪያቸው ነው። የመጡበት በዋነኝነት ከስር እያደጉ እድገት እየተሰጣቸው ከሆነ ተረግጠው ተጨቁነው ነው ያለፉት..በጣም አጋነው ሲቆጡ እኔ በበኩሌ እስቃለሁ😂 ሰውየው አበደ እንዴ የሱ ጤነኛ አለመሆን የሚታየኝ ሁሉም ሰው ዋጋ ያስከፈለው ታሪክ አለ ያ ያልታከመ ቁስል ነው። እንግዲህ ያገኙት ሰው ላይ የሚወጡት በክፉ ነገር ውስጥ መልካም ነገር አለ። ነገሩን ተቀብለህ መልካም ጎኑን ተመልከት ከቦታ ቦታ ብትቀይር ምናልባትም ምንም ለውጥ ላይኖር ይችላል። አለቃዬ የሚቆጣኝ ሁሉ ነገር ልክ ነው ብለህም ሙሉ ለሙሉ አትቀበል አትመን የሚያወራውን እያንዳንዱን ነገር ታዘበው..አንዳንዴም እኛን የሚይዙበት አሳጥተናቸው በምን ልጉዳ ልቅጣ ብሎ ኮ በማያገባው በግል ህይወትህ ሁሉ ይገባል። ስራን ሁሉ ወስደው አበላሽተው የሚሰሩ አለቆች አሉ አንተ የምትጠየቅበትን። አለቃህ ነው ግግም ይላል እንደው የሆነ ሰዓትማ ጠዋት ስትገባ ቦታ ላይ ተቀምጦ ሰርፕራይዝ ያደርግሃል አንተ ደግሞ በተራህ የእሱ ቦታላይ😂 😂 .. ለማንኛውም የሚሆነውን ተቀበል(በሚሆነው ነገር አትረበሽ) ፣ ታዘብ፣ ራስህን አረጋጋ ፣አወንታዊ አመለካከት ይኑርህ ፣ አትፍረድ፣ አትጥላ..
Aug 30, 2025