እስኪ ስለኔ የሚሰማቹን ንገሩኝ 🙏😢 22 አመተ የሞላኝ በቅርቡ ነው የቴክኒክ ተማሪ ነኝ በትምህርት ትንሽ ደከም ያልኩ ነኝ ምንም ሙያም የለኝም ለ 4 አመት ሱስ ውስጥ ነበርኩኝ ከሱስ ለመዳን ከ 4 ወር በላይ በፀበል ጂም በመስራት በብዙ ችግር አሳለፍኩ ግን ልፋቴ በቂ አይደለም 😭 አሁንም ስለ ስራ እና ስለ ትምህርት ሳስብ ገና እሩቅ እንደሆነ ይሰማኛል ጊዜው የረፈደ መስሎ ይሰማኛል ሬሴን ለማጥፋት 80% ላይ ደርሼ ነበር ግን በየጊዜው ሀሳቤ ይለዋወጣል እና ምን ላድርግ እባካቹ ምከሩኝ ተሰቃየሁ 😭
Aug 25, 2025Calm down boy. ሁላችንም ከሞላ ጎደል እያለፍንበት ያለነው ነገር ነው። Social crisis ኢትዮ ላይ መከሰቱን የምትስተው አይመስለኝም። በተለይ ማህበራዊ ሚዲያ ያመጣው መቃወስ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም። ሌሎች የተሳካላቸው አንተ ደግሞ በጣም ወደ ኋላ የቀረህ እንዲመስልህ የሚያደርግ ነገር በብዛት ተዛምቷል። በቅድሚያ ወደ ራስህ ተመለስ። ከሱስ በመውጣትህ ብቻ ትልቅ ነገር ማሳካትህን ማወቅ አለብህ። ገና 'ኮ መኖር አልጀመርክም። ትኩረትህን በየቦታው አትበትነው። እራስህን ሰብስበህ ግብህ ላይ አተኩር። ሌላው ደግሞ ምንም እንኳን ባይነፋም መኖር ካለ መኖር የተሻለ ነው። እራስህን ስለ ማጥፋት ማሰብ በራሱ ችግሮችን ለመገዳደር ወኔ በማጣት የሚመጣ የሽንፈት ፅዋ ነው። እራስ አገዝ መፃሕፍትን አንብብ፣ስፖርት ስራ፣በእምነትህ ጠንክር፣በአቋራጭ ለማደግ የምታደርገውን ሩጫ አቁም። There is no shortcut. Work hard and smart. Learn new skills that will earn u money. Got u man🙂.
Aug 25, 2025