በቅንነት መልሱልኝ ትልቅ ጉዳይ ነው:: ጓደኛ አለችኝ እና ስራ ነበራት ስራውን ትታ ለወደፊት ሕይወታችን ጥሩ ገቢ ማግኘት አለብን ብላ አረብ አገር ለመሄድ ፕሮሰስ ጀመረች በዝህ መሀል አንድ ቀን አብረን ዋልን ግንኙነት አረግን መድሀንት ሰጠዋት ዋጠችሁ ከዛ ፕሮሰሱን ጀመረች ከወር ቡኃላ የወር አበባዬ ቀረ አለች ቼክ ስናረግ እርጉዝ ናት ምን ላድርግ? ዕቅዳችን 2020 መጋባት ነበር:: ያለ ዕቅዳችን ልጅ መጣ ላስወርደው ቤተሰቦቼ ይገሉኛል አለች እኔ ደግሞ ቤተሰቦችሽ ልጅ ከሰጠሽ አምላክ አይበልጡም ስለዝህ ምንም እንዳታደርግው ውለጅው አልኳት እንደምንም ለእናቷ ነገረች ለካ እናቷ በሁኔታዋ ያውቁ ነበር ለወንድሞቿ አልተነገራቸውም ለእህቷ ብቻ ነው የተነገራት ከዛ ማዘሯ ሽማግሌ ይላክ አሉ:: ምን ማድረግ ነበረብኝ እንድታስወርድ ወይስ ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰንኩት? አሁን ላይ እኔ ጥሩ ገቢ አለኝ በዝህ ሁኔታ አልነበረም ማግባት የፈለኩት ግን የእርሱ ፍቃድ ነው ብዬ ተቀበልኩት::ግን በጣም እየተጨነኩ ነው እውነት ለመናገር 😟😔😔
Aug 25, 2025ብሮ ሽማግሌ ላክ በቃ እርሱ ያለው ነው የሚሆን ጥሩ ገቢም ካለህ ጥሩ ነው ልጅ የራሱን በረከት ይዞ ይመጣል ይላሉ
Aug 25, 2025