ሠላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ! መፍትሔ ጠቁሙኝ እስኪ ባለቤቴ ከልጅነቷ ጀምሮ ሠው እጅግ ትፈራለች ፤ በህጻንነቷ ዘመድ መጥቶ ሲስማት ትፈራለች ታለቅሳለች ፤ ሌላው ቀርቶ ከብት እንኳ ሲጮህ ትሸሸጋለች ፤ እናቷ እንኳን ሊያስነጥሳት ከሆነ እንዳትደነግጭ ብላ ቀድማ ትነግራታለች። የምርቃቷ ጊዜ ከቤት ዉስጥ ሠው እየተጫወተ ፈርታ እሷ ጓዳ ነበረች። አሁን ራሱ ድንገት ጮክ ብዬ ከተናገርሁ ወይም ሳታስበው ከነካኋት ትደነግጣለች። እንኳንና ሌላ ሰው እናቷ ከቤታችን ብትመጣ ትሳቀቃለች። አብሶ ሌላ ሠው (ለምሳሌ የእኔ ቤተሰብ) ይመጣል ካልኳትማ በጣም ሃሣብ ይያዛታል : ትጨነቃለች : እንቅልፍ ሁሉ አይወስዳትም : ባስ ሲል ደግሞ ጥለሽ ሂጂ ራስሽን አጥፊ የሚል ስሜት ያስቸግራታል ፤ እንዲህ ከምጨናነቅ አንተም በዚህ ተፈጥሮየ ከምትቸገር ባላገባ ይሻል ነበር ትላለች። እስኪ የመፍትሄ ሃሣብ አጋሩኝ። በሠላም ዋሉ!
Aug 17, 2025If it is sth related to childhood trauma it's better to see a therapist Lemnum lemnum gn bedenb tsebel ttemek. Wedefetari mekreb lehulum neger mefthe alew🙌
Aug 17, 2025