Selam guys 23 M Be 23 ametachu ke fam arif birr bisetachu like wurs ,mn taregubetalachu eske 500k bihon biru mn taregubet neber ? Ye gibi temari negn thanks
Aug 12, 2025ከትምህርትህ እንዳያርቅህ ቀለል ያለ ነገር ግን ቢያንስ ጊቢ ሳለህ የሚያስፈልግህን የወጪ ገንዘብ Generate የሚያደርግልህ ነገር... - 1. አንድ የቸገራትን ነገር ግን አሪፍ ሞያ ያላትን ሴት ፈለግ ፈለግ አድርገህ ካገኘህ በኋላ ቡና ቤት ትከፍታለህ። ("ለምን ሴት መረጥክ?" የምትሉ ፌሚኒስቶች እንዳትቸኩሉብኝ አደራ። ምክንያቴን ከታች እጽፈዋለሁ።) "ተማሪ ቡና አይጠጣም" የሚለው አባባል ለቋንቋ ክፍል (ምሳሌያዊ አነጋገር) ከመዋል ያለፈ እውነት የለውም። መሬት ላይ ተቃራኒው ነው ያለው። ተማሪ ያለ ቡና 🙅🏽♂! ቡና ቤቱን ስትከፍት ጊቢ አካባቢ ያለ መሆን አለበት። ከጊቢ ከራቀ ተማሪው ላይመጣልህ ይችላል። ከባህላዊ መንገድ ባሻገር ዘመናዊ ነገሮችን ጨማምር። (ይህን መዘርዘር ከጀመርኩ ሐሳብ ይሰፋብኛል። ወስነህበት ዝርዝር ከፈለግክ ሌላ ጊዜ እጽፍልሃለሁ።) ጎበዝ ከሆንክ ብሩን ከመቁጠር አልፈህ መካከለኛ ገቢ ያለው፤ እንደ አገራችን የጊቢ ተማሪዎች ከማለቃቀስ አልፈህ ሌሎችን ረጂ ትሆናለህ። ሴት የመረጥኩበት ምክንያት 1. በአገራችንም ሆነ በሌሎች አገራት የጉልበት ስራ ላይ አነስተኛ ክፍያ የሚጠይቁት ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ናቸው። 2. ብዙ ጊዜ አብረው/ተጠግተው ስለሚኖሩ የወጪ መጋራት ላይ ናቸው። ይህን በምሳሌ ስናየው.. አንዷ በ2000 ብር ቤት ብትከራይ ምናልባት ጓደኛዋ ጋር አንድ ላይ ለመኖር ተስማምታ 1000 ብሩን ጓደኛዋ እየከፈለች ነው። ከጓደኛ ካልሆነ ባለትዳር ትሆናለች። ስለዚህ ባሏን ለማገዝ ብላ መስራት የምትፈልግ ትሆናለች። 3. በአገራችን የቡናን ስራ ከወንድ ይልቅ ሴቷ በደንብ ትሰራዋለች። -2. ሌላ ስራ.. እዚያው ጊቢ አካባቢ ለቁጥጥር የሚመችህ ስራ... ፈቃድ አውጥተህ ኮፒ ቤት መክፈት። ከያዝከው ብር ከፍ ሊልብህ ይችላል። ግን ጎበዝ ከሆንክ (Gobez in a sense: being the best resource economiser!) አትራፊ ትሆናለህ። -3. ሌላ ስራ.. ስልክና pc እየገዛህ መሸጥ። የዘመኑ ተማሪ ያለ ስልክ እና ኮምፒውተር መማር አይችልም። ይህን ስራ በራስህ + በትርፍ ጊዜህ ስለምትሰራው የተቀጣሪ እና የጊዜ እጥረት ጣጣ አይኖርብህም። This job is risky, but if you manage the risks, you will have a good pocketed money. -4. ፈጣን ምግብ ቤት (Fast food) መክፈት ከጤና አኳያ ፈጣን ምግብ ባይመከርም ከጊቢ ምግብ በጣም ይሻላል!🙂 እዚያው ጊቢ አካባቢ ከፍተህ መስራት ትችላለህ። እንደውም ጎበዝ ከሆንክ እና ከጊቢው ፈቃድ ካገኘህ (ግን አታገኝም) ተጨማሪ ሶስተኛ ሰው ቀጥረህ delivery እንዲሰራልህ ታደርገዋለህ። ዶርም ድረስ እያደረሰ የምግቡንና ያደረሰበትን ሒሳብ የሚቀበል አንድ ሰው ይኖርሃል። የምግብህን ትቀበላለህ። የ deliveryውን ደግሞ 50% ትካፈላለህ ወይም ለልጁ ትተወዋለህ። ቀሪውን ሌሎች ይጨምሩልህ። ለጊዜው የመጣልኝ ሐሳብ ይህ ነው። ማወቅ ያለብህ የአዋጭነት ጥናት መስራት እንዳለብህ ነው። ጊቢ ውስጥ እና ከጊቢ ውጭ ተማሪው ምን እንደሚፈልግ በደንብ አጣራ። ደህና ዋል።
Aug 13, 2025