ሰሞኑን ይሄን ሁለት ቀን ጆርዲ ስለምትባለው ሳትሰሙ/ሳታዩ አትቀሩም ብዬ እገምታለሁ፤ የእኛ ሀገር ገና በእንደዚህ አይነት ሽፋን ተመሳስለው በተደበቀ የሴራ እሳቤ የሚመጡ ሰዎችን ለመረዳት ገና ይቀረናል ወይ ደግሞ ሳንረዳው ነገሩን እናራግበዋለን፤ lgbtq+ የሚባሉት አካላት በብዙ መልኩ ነው የሚመጡት፤ ከእነዚህ ውስጥም አንደኛው መንገድ Social Media ነው (በተለይ ደግሞ tiktok)፨ ለሴቷ በወንድ ምክንያት እየተገፋችና ብዙ በደል እየደረሰባት እንደሆነ የሚያሳዩ ምስሎችን ያቀርብላታል፣ በተቃራኒው ደግሞ ለወንዱ ሴቶች ምንም ሳይለፉ እንደሚኖሩና ተቀምጠው ብቻ ወንዱን እንደሚተቹ እይነት ምስል አሪፍ በሚመስል መልኩ ያቀርብለታል፣ በዚህም ዋነኛ አላማቸው ሴቷን ከወንዱ፣ ወንዱን ደግሞ ከሴቷ የማቃቃር/የማራራቅ ብቻ አይደለም፡ እሱን ተጠቅመው ሴት ከሴት ወንዱን ደግሞ ከወንዱ ሌላ ቅዱስ ቃሉ ወደ ማይፈቅደው ርካሽ እቅዳቸው መሳብ ወይም የረከሰ አላማቸውን ማስፈፀም ነው፤ እና ምን ልላቹ ፈልጌ ነው፥ ሀገራችን ላይ ብዙ ችግር እንዳለ ግልፅ ነው ግን የእኛን ችግር በራሳችን መንገድ ነው መፍታት ያለብን እንጂ ስልጣኔ እየመሰለን ከውጭ የሚመጡ አስተሳሰቦችን እንደወረደ ለመቀበል ባንቸኩል ጥሩ ይመስለኛል፣ ሀሳቤን ለማስረዳት በደንብ ብፅፍ ደስ ይለኝ ነበረ ግን ቦቱ አይፈቅድም፣ ምን አልባት በቀጣይ እመለሳለሁ፣ እስከዛ የእናንተን ሀሳብ ብትፅፉ ደስ ይለኛል🙏
Aug 06, 2025ሳንወሻሽ ምን እንደበከለን ታቃለህ?? ምናያቸው የውጪ ፊልሞች ናቸው ። እንደቀላል ነገር አይተን እኛን ወጣቶቹን ቀይረው አሁን የህፃናት ፊልሞች ላይ ማምጣት ጀምረዋል። ባለፈው እንደ ድንገት አይቼ ማመን ነው ያቃተኝ። ወገን ውሀ ሲወስድ ያሳሳቀ ነው ቆም ብለን ካላሰብን ነገ ምንወልደው ልጅ ወንድ ከወንድ እያለ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸው አይቀርም እንደግል ሁላችንም ቆም ብለን ካሰብን እንደ ማስ እየበዛን እንመጣለን🙌
Aug 06, 2025