የጉሊት እናት መቀነቷን አጥብቃ ለልጆቿ ብላ ኑሮን ለማሸነፍ የማይቻል ችላ ከጠዋት እስከ ማታ እንጀራ ፍለጋ ነገዋን ልትሰራ ጉልበቷ ሚተጋ ብርቱ ሴት አንድ አለች ጥቂት እቃ ይዛ መንገድ ዳር የዋለች፡፡ ዝናብ ሳያግዳት ሀሩር ሳይበግራት ቁርስ እንኳ ሳትበላ ለልጆቿ እራት ግልምጫው፣አሽሙሩ፣ሁሉን ተቋቁማ በውድድር አለም ጨለማውን ቀድማ ጎህ ሳይቀድ ወጥታ የምትገባ ሌሊት ምስኪን እናት አለች የምትውል ጉሊት፡፡ ምንም ባታተርፍም ከባህሏ ሳትርቅ ፍቅሯንና እቃ አብራ የምትመርቅ የውስጧን አምቃ፣ በጥርሷ ደብቃ፣ ትልቅ ህልም ሰንቃ፤ ውላ የምትገባ በጥቂት ቸርችራ ዕድሜዋን ሰውታ ቀልጣ ምታበራ ከጉሊት መንደር ላይ አለች የሴት አውራ፡፡ by @Abuugida
Aug 06, 2025