Marketing and sales management lemar nber Ana bzi Zerf yalachu Endat nw sera agenbetalew
Aug 06, 2025"እንዴት ነው ስራ አገኝበታለሁ?" ተብሎ አይጠየቅም እኮ። ትምህርቱ ለስራ ማዋጣቱን ሳይሆን አንተ ለስራው ብቁ ነህ ወይ? ነው ጥያቄው። ትምህርትን ስትማር "በዚህ ሰርቼ ገንዘብ እይዝበታለሁ።" የሚለውን ሐሳብ ብቻ aim አድርገህ መማር የለብህም። ለምን መሰለህ እንዲህ የምልህ? አንተ ገንዘብን ትኩረት አድርገህ ስትማር እውቀቱን ችላ ትለዋለህ። "ይህን ተምሬ ገንዘብ እይዛለሁ።" ብለህ ስታስብ "ስራውን በትክክል ሰርቼዋለሁ ወይ?" የሚለውን መሠረታዊ የስራ ሀላፊነት ትረሳዋለህ። ቀጣሪህ "ምን ያህል እከፍለዋለሁ?" ብሎ አይጨነቅልህም! "ምን ያህል አሳምሮ ይሰራልኛል፣ ታማኝ ሰራተኛ ከየት ላግኝ?" ነው ጭንቀቱ! አንተ አሳምረህ ከሰራህለት የገንዘቡ ጉዳይ አያሳስብም። የሚገባህን ይሰጥሃል። አንተ በተማርከው ነገር ከቀጣሪህ ገንዘብ መቀበልን ብቻ ስታስብ ቀጣሪህ ደግሞ ካንተ ለቦታው/ስራው የሚሆን ትክክለኛ እውቀትን ይሻል። በዚህ ጊዜ መስመር ትተላለፋላችሁ። ከአጻጻፍህ ራስህን ስራ ፈጣሪ ሳይሆን ተቀጣሪ ለማድረግም ጭምር ነው የምትማረው። ስለዚህ ተቀጣሪ ስትሆን መማርህ ብቻ በቂ አይደለም። የመጠቀ ዕውቀት መጨበጥህ ግድ ነው። ዘመኑ በህገ-ወጡም በህጋዊውም መንገድ ፉክክር የበዛበት ነው። (ህገ-ወጥን እንደማልመክርህ ታውቃለህ-አለፍኩት!) በህጋዊ መንገድ ስትጓዝ አንተ ለመቀጠር ብለህ ተምረህ CVህን ስታስገባ አንዱ ደግሞ ስኪሉን ማስተር አድርጎ CVውን ያስገባል። አንተን ውሃ በላህ። So my advice for you is "Do not be money-focused. Be skill-focused." በዚህ ጊዜ ስራው ወዳንተ ይመጣል እንጂ አንተ ወደ ስራው አትሄድም። የመጨረሻው ምክሬ ከ Hard skills ባሻገር Soft skills የሚባሉትን አዳብር። ግማሹን የስራ እና የህይወትህን መስመር ያስተካክልልሃል። ሰንብት በሰላም
Aug 06, 2025