Protestant church ከመሄዴ በፊት እስቲ አንድ አንድ ጥያቄዎችን ልጠይቅ። 1) 1ኛ ዮሐ 1:2 ? ክርስቶስ የዘለአለም ሊቀ ካህን ነው።የሊቀ ካህን አንዱ ስራ ደግሞ ምልጃ ነው & ክርስቶስ በጥፊ መመታቱ፣ጋኔን አለብህ መባሉ ከአብ ያላሳነሰው እንዴት ማማለዱ ከአብ ያሳንሰዋል? 2) ሐይማኖት እንዴት ነው የሚያድነው? ቅዱስ ጴጥሮስ,ዮሐንስ,ጳውሎስ...ኦርቶዶክስ ነበሩ ወይንስ ፔንጤ or Adventist...?(ብንፀድቅም ባንፀድቅም እንኳንም ኦርቶዶክስ ሆንኩ ያሉ አንድ አባት ንግግር ሰምቼ አፈርኩ) 3) እንዴት አንድ ቅዱስ መልአክ ከክርስቶስ ፣ ከሀጢአት በቀር እንደእኔ የተንገላታው ክርስቶስ በላይ ይራራልኛል? ቅዱስ ገብርኤልኮ የስቅለት ቀን የሰው ልጆች ድህነት ቀን ተናዶ ሰይፉን ሊወረውር ነበር(የሚል ት/ት አለ ኦርቶዶክስ church) አመሰግናለሁ።በትህትና መልሱልኝ።
Jul 31, 20251ኛ ዮሐንስ 5:20 እየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ እና የዘላለም ህይወት ነው....ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ አለምን ከእራሱ ጋር አስታርቋል ...¹⁸ ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ ¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። ²⁰ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።....ከፕሮቴስታንት ሀይማኖት በፊት የነበሩት ሃዋሪያት አልዳኑም ማለት ነው?? ምክንያቱም ሀይማኖቱ ከዛሬ 400 መቶ አመት በፊት ነው ታዳ 1600 አመተ ምህረት በፊት የነበሩት ሀዋሪያት እና ቅዱሳን አልዳኑም እናቱስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያምስ?? ሲቀጥል ሀይማኖት አያድንም ማለትኮ አስተመህሮ ነው አይደል አስተምህሮ የሌለው አንድ እምነት ንገረኝ እስኪኪ??
Aug 01, 2025