Hi 👋 Amharic lboled metshafochn this past 2 years yewetutn(at least 10) ena Orthodox menfesawi metshafochenm suggest argugn Tnx
Jul 22, 2025ልቦለድ ብዙም አደለሁም ግን ታለ የአለማየሁ ገላጋይ፣ሰመመን እና ግራጫ ቃጭሎች are the best so far ከመንፈሳዊ ደሞ የሆነ ጊዜ ለአንድ ሰው መልሼ የነበረው... *መድሎተ ጽድቅ-ለክርስትና መሠረት የሚባሉ ነገሮች ሁሉ አሉበት...ባልሳሳት 2 ቅጾች አሉት ጌራ መድኃኒት-ወልደ አብ ለማባለው መጽሐፍ ምላሽ የተሰጠበት(ለቅባቶች) የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ- ከክርስቶስ ትንሳኤ በኋላ የቤተክርስቲያን ታሪክ ምን እንደሚመስል የያዘ መጽሐፍ(ስለ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት refer ማረግ ከፈለክ አንብበው) ማስያስ-basic theological ሐሳቦች የያዘ ወይም ለtheology ጥሩ መነሻ የሚያሲዝ ምርጥ መጽሐፍ ውሥጡ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ፣ሥጋዌ...ስለ ሥነ ፍጥረት...ስለ አመክንዮ እና እምነት ወዘተ አሉበት...highly recommended መጽሐፈ አክሲማሮስ-ስለ ሥነ ፍጥረት በአጠቃላይ የያዘ መጽሐፍ ነው...በጣም ደስ የሚል መጽሐፍ ለኔ የመንፈሳዊ መጻሕፍትን ማንበብ ስጀምር በዚ ነው የጀመርኩት ሕማማት-ክርስቶስ ላይ የደረሰውን መከራ ከዕለተ ሐሙስ ምሽት እስከ አርብ 9 ሰዓት ድረስ ያሉትን የያዘ ነው ከነድንቅ ምሥጢራቸው ጭምር(must case) ወልታ ጽድቅ-ስለ ጥንተ አብሶ እና ስለ ደቀ-እስጢፋ(estiphanosites) ታሪክ ምናምን ያለበት @polymathlads እዚ የፈለከውን መጽሐፍ ጠይቅ ካለ ይላካል
Jul 22, 2025