መንግስት ግን ምን አርጉ ነው ያለን? ሌላ ሌላው ይቅርና ኑሮ ውድነቱን ጫፍ ማድረሱ ሳያንስ እንደገና ደግሞ በስንት አይነት መልኩ ነው የሚመጣብን፣ የማብራትና የውሃ ክፍያ ላይ የተደረገውን ጭማሪ መቼም እስካሁን ሳታውቁት አትቀሩም በዛ ላይ ገና ካሁን በኋላም በየዓመቱ እየጨመረ ነው የሚሄደው ተብሏል፣ የሕዝቡ ገቢ ሳይስተካከል የግብሩን መጠን ጨመረው እነ IMF እንዳዘዙት፣ ከቤት አከራዮችም ጋር መጣ፣ Online ለሚሰሩትም ግብር ተዘጋጅቷል፣ ቲክቶክና ዩቲዩብ ለሚሰሩትም አልቀረም፣ ከBybit ላይ የኢትዮጵያ ብር እንዲወጣ አስደርጓል፣ በሂደት ሌሎቹንም ማስቀረቱ አይቀርም፣ የማይጠየቅ የግብር አይነት የለም እና ቆይ ምንም የስራ አማራጭ በሌለበት ሀገር ላይ ወጣቱ ምን እንዲሆን ነው የፈለገው፣ አለ የተባለውን አማራጭ በመሉ ይዘጋል፣ የግድ ሁሉም ሌባና አጋች ሆኖ እንዲቀር ነው የፈለጉት ወይስ ምንድነው ቆይ ግራ አጋባን እኮ፣ ዝም አሉ ተብሎ እንዴት የገዛ ሕዝቡን በዚህ ደረጃ ይፈታተናል?
Jul 18, 2025Simeslegn dehan ke mdritua matfat new alamaw😭
Jul 18, 2025