የሀገራችንን የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ልብ ብላችሁ ታውቃላችሁ? ፍፁም ከእውነት የራቀ ፤ ለህዝብ ከማሰብ ይልቅ የራስን ሀብት ማግበስበስ ላነዘይ ያተኮረ፤ አጉል ማታለል ሆኗል።አራት ዲጂት ቁጥር ይናገርና ወደዚህ ቁጥር ok ብለው ይላኩ እና English and Chinese ቋንቋዎችን ይማሩ ይላል።አስቡት ኢትዮጵያ ውስጥ ከ ነርሰሪ እስከ MBA ድረስ ተምረው ለማውራት የሚያዳግታቸው english እና አለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች ሁሉ ከባድ የሚባለውን መንደሪን ቋንቋ እነሱ በ text ሊያስተምሩ።ሊያውም በቀን 3-5 ብር እየቀፈሉ።አንዳንዶቹ ደሞ ወደ ok ብለው ይላኩና 100k ብር ይሸለሙ ይላል።ደሞ አነጋገራቸው እኮ ገንዘቡን በዕድል ሳይሆን በእርግጠኝነት(100%) እንደሚያገኙት የሚያስመስሉበት መንገድ።እንደገና የህዝቡን በዝች ሀገር መማረር እና ተስፋ መቁረጥ በሚገባ ስለተረዱት ወደ ok ብለው ይላኩና ዱባይ ይሂዱ ይላል።በቴሌግራም እና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች እንደልብ የሚገኙትን (scholarship address) ታገኛላቹ ይላሉ።ቆይ ከአልኮል መጠጥ እና ከእነዚህን መሰል ማስታወቂያዎች የቱን ነበር ማገድ የሚገባው? ተመልከቱ እስቲ የነጮቹን ማስታወቂያ ስለምን እያስተዋወቁ እንደሆነ እራሱ አይታወቅም። ከሞላ ጎደል ምንም ማጋነን የለውም።ቆይ ይህንን የሚቆጣጠር ህግ የለም እንዴ??
Jul 17, 2025በሐሳብህ እስማማለሁ። ነገር ግን የመጠጥን ማስታወቂያ ማገዳቸው በየትኛውም መሥፈርት ስህተት የለውም። እነዚህ በቴክስት የሚላኩ የተጋነኑ ማስታወቂያዎችን ለማጋነን ብለህ የመጠጧን ማስታወቂያ ማራከስህ ቦታ የለውም። እናውራ ከተባለም በተጋነነው የቴክስት ማስታወቂያ ብር ከመቀፈል ('ቀ' ይጠብቃል) ያለፈ አንድም ነፍስ ሲጠፋ አላየንም። ነገር ግን ባራከስከው የመጠጥ ማስታወቂያ ከትንሽ እስከ ትልቅ ወንጀል ተሰርቶ አለፍ ሲል የሰው ነፍስ የሚጠፋበት ነው። የምናየውን አናስተባብልም። በሐሳብህ እስማማለሁ። የቴክስት ማስታወቂያቸውን ለማጋነን ብለህ የመጠጡን ማስታወቂያ ማራከስህን አልስማማበትም። በመጠጥ ማስታወቂያ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ትውልድን ለመታደግ የበኩሉን ለተወጣው ለቀድሞ የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዶክተር አሚር አማን ምስጋና ይድረሰው። (እሱ ባያነበውም ተመስግኗል!) በእነዚህ ማስታወቂያዎችም እርምጃ ለመውሰድ አንድ እርምጃ የሚራመድ አሳቢ ሰው እንደምናገኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
Jul 17, 2025