Orthodox አማኝ ያልሆነ ሰው ቤተ መቅደስ መግባት ይችላል? እንዲሁም ደሞ ህፃን ልጆችን ውስጥ ገብቶ ማስቆረብ ይችላል? Please ke ትህትና gar melsulgn🙏☺️ endihum demo lemsetugn mels amesegnalew🫶🏽
Jul 13, 2025ውስጥ መግባት ይችላል ግን ፍሬ ቅዳሴ የሚለው ክፍል እስኪደርስ ብቻ ነው ቅዳሴ መሳተፍ የሚቻለው ወይንም ዲያቆኑ ጻኡ ንዑሰ ክርስቲያን(የክርስቲያን ታናናሾች ውጡ) ባለ ጊዜ ከቤተ መቅደስ መውጣት ይገባል እሊህ የክርስቲያን ታናናሾች የተባሉት ገና ጥምቀተ ክርስትናን ያልተቀበሉ ነገር ግን በመማር ላይ ያሉ ናቸው ለምን ይወጣሉ?ምክንያቱም ገጻ በኋላ ያለው ሥርዓት ለነሱ እንዲያዩ አይገባምና(ኅብስቱ ወደ ክርስቶስ አማናዊ ሥጋ ወይኑ ወደ ክርስቶስ አማናዊ ደም የሚለወጥ በመሆኑ እና እነዛ ንኡስ የተባሉት ደሞ ይሄን ምሥጢር ስለማይገባቸው(ላልቶ) ነው ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አላደረባቸውምና(በጥምቀት) ኅጻን ልጆች ማለት ከሌላ ቤተ እምነት ያሉ ናቸው? እንደዛ ከሆነ ፍጹም ስህተት ነው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ከናንተ አንዱ ሳይገባውና ሳይገባው(ጠብቆና ላልቶ) የክርስቶስን ሥጋ እና ደም የተቀበለ ዕዳ በደል እንዳለበት ጽፎልናል ስለዚህ ከሌላ ቤተእምነት ከሆነ ክልክል ነው ተለቅ ያሉ ሰዎች ከሆኑ ደሞ ንስሐ ተቀብለው ቀኖናቸውን ፈጽመው ያንን ምሥጢር መፈጸም ይችላሉ
Jul 14, 2025