ሰላም fam እስኪ ሰፈር ውስጥ በትንሽ ገንዘብ ልሰራቸው የምችላቸውን business ንገሩኝ ቁጭ ከምል ለስራ like አትክልት ጉሊት ነገር እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ 🙏
Jul 09, 2025Movie ማከራየት ጀምር። እስከ 25K Birr ባጀት ካለህ። Desktop Used ( ጥቃም ) እስከ 12K Birr ግዛ። የሌለ እንዳይመስልህ አለ። 3k Birr Speaker ጥቃም። አዲስም ሊኖር ይችላል። 3k birr ኪራይ ታገኛለህ? Movie መጫን ትችላለህ። አዲዲስ "ትምህርቶችን ታገኛላቹህ" ብለህ እየለጠፍክ መሸጥ ትችላለህ። ለምሳሌ: ሞሽን ዲዛይን መማር ሚፈልጉ ብዙ ወጣቶች አሉ ፣ ቪድዮ ኤዲቲንግ መማር የሚፈልጉ ፣ ግራፊክስ ዲዛይን ፣ ዲጂታል ማርኬቲንግ ወዘተ ቪድዮዎችን መጀመርያ ዩቲዩብ ላይ ፣ ክራክድ የተደረጉ ቲቶሪያሎችን ሰብስበህ መሸጥ። ሌሎቹ በአካል እናስተምራለን ብለው ገንዘብ ሲበስቡ አንተ በአጭሩ ሰዎችን እየረዳህ እራስህን በትንሹ ታሳድጋለህ። ቢዝነስ ጀመርክ! በዚህ መሀል አንተ ብቃት ( ሙያ ) መማር አለብህ። ከላይ የተዘረዘሩት በፈጣኑ መማር የምትችላለቸው ናቸው። በአሁን ሰአት ከአሁን በኋላ በኢትዮጵያ ሊሰራባቸው የሚችሉ ጠንካራ የማይናቁ ትምህርቶች ናቸው። በሶሻል ሚዲያው አሁን የኢትዮጵያ ድርጅቶች ስራቸውን አጧጡፈውታል። የጤና ድርጅቶች ፣ የፈርኒቸር ፣ የውበት ትምህርትቤቶች ወዘተ አሁን ገንዘብ የሚያገኙት ከሶሻል ሚድያ አይተው በሚመጡ ሰዎች ሆኗል። እነዚህ ድርጅቶች ማን ያስፈልጋቸዋል? ቪድዮ ኤዲተሮች ወዘተ። ስለዚ እግረመንገድ ሙያ መማር አለብህ። አፍሪወርክ ኢትዮጵያ የተባለው የቴሌግራም ስራ ቀጣሪ ላይ የሚለቀቁ ስራዎች በቀን ውስጥ ከላይ የተዘረዘሩት ስራዎች ከ 10 ይበልጣሉ። በወር እስከ 300 ስራዎች ይለቀቃሉ በዚህ ሙያ ውስጥ። ቢያንስ ቤትህ ሆነህ ለ 10 ሰው መስራት ከጀመርክ እንዳንተ ጌታ የለም።
Jul 10, 2025