ሰዎች ብቻ የመሆን ሱስ አለ እንዴ ወገን? ብቸኝነት አይሰማኝም ግን በቃ 24/7 ብቻዬን ነኝ። ወክ ማረገው ብቻዬን ቤተክርስቲያን ብቻዬን ሆቴል ካፌ ምናምን ብቻዬን ካመመኝም ሆስፒታል ምሄደው ብቻዬን ክላስ ምቀመጠው ጥግ ላይ ብቻዬን😂 ችግር ይኖረዋል ወይ? እኔ ተመችቶኛል ይሄ ባህሪዬ ግን ተይ የሚሉኝ እንደ ምድር አሸዋ በዛብኝ ቁጥራቸው
Jul 08, 2025ይሄ ከአለም ህዝብ ቁጥር ጥቂቶች የታደሉት ፀጋ ነው። ሰላም እና እረፍትም ጭምር ነው። ኢነርጂ ነው። በህይወታቸው በራሳቸው መቆም የማይችሉ ሰው ባይኖር የሚጨንቃቸው ራሳቸውን ችግሮቻቸውን መጋፈጥ የማይችሉ ደካማ ሰዎች ምክር እየሰማሽ ራስሽን አትበጥብጪ ላንቺ ከተመቸሽ የማንም አስተያየት አያስፈልግሽም😊 አንቺ እንደዛ ስትሆኚ ልክ ያልመሰለው ሰው ያለ ሰው የማይኖር በይሉኝታ የተከበበ ለራሱ ፍቅርም ጊዜም የሌለው ሰነፍ ሰው ጥሎት ቢሄድ በር ዘግቶ ለማልቀስ ክብር ያልበቃ ከሰውየው እግር ስር ተንበርክኮ አትሂድ ብቻዬን ነኝ እያለ እየለመነ የሚኖር ሰዎች በእሱ ላይ ቢረማመዱ የሚያለጠልጥ ራሱን ያልሆነ ለጥቅም የሞተ ሙታን ነው። አንቺ ምን ቦጣሽ እና እንዲህ ትሆኚ?🤔
Jul 08, 2025