ሰላም ትላንትና ማታ ነበር ጀሞ ኣከባቢ ከስራ ስመለስ በጣም መሽቶ ነበር እና ቤቴም ትንሽ ወጣ ያለች ቦታ ነው እና ብዙ መታጠፊያዎች ኣሉት ከዚያ በኣንዱ መታጠፊያ ስደርስ የሆነች ኣጭር ቀይ ቀሚስ የለበሰች ሴት ጥቁር ቦርሳዋን ይዛ ወድኔ መራመድ ጀመረች በዚያ ብርድ ምንም ኣልመሰላትም ሂዉማን ሄሩኣ ጆሮ ጌጯ በጣም ረጅም ነው እዚህ ላይ ምን የሚያህል ሂል ጫማ ተጫምታለች ። ትንሽ ወደኔ ከተራመደች በዋላ እርምጃዋ ወደ ሩጫ ተቀረና ሮጣ መጥታ ስስ ብልቴን መታቺኝና ቦርሳዋን ኣስታቅፋኝ በኣንደኛዉ መታጠፊያ እየሮጠች ሄደች እኔም በጣም መቆም ኣቅቶኝ ከሰዉ ግርግዳ ስር ሽጉጥ ብዬ ተቀመጥኩ ከዚያ ሁለት ጥቁር ሱፍ የለበሱ ወጠምሾች እየሮጡ መጡ ኣንዱም ሲያየኝ መጣና ሲጥ አድርግ ኣነቀኝ ከዛ ከእንቅልፌ ብንን ብዬ ተነሳው እባካችሁ ህልም መፍታት ምትችሉ ተባበሩኝ 🙏
Jul 04, 2025ፊልም አታብዛ ትቃወሳለህ😒
Jul 04, 2025