ሰላም ቤተሰብ አንድ ግራ ያጋባኝ ሀሳብ ነበር ፣አንድ ጓደኛዬ ነበር እና ትንሽ ጁስ ቤት ከፍቶ እየሰራ ነበር መሀል ለይ በአንዳንድ ምክንያቶች ከስሮ (ከሰው ብድርም አጥቶ) ሊዘጋው ሲል እኔ ትንሽ ብር አበደርኩትና አሁን ስራ እየተስተካከለለት ነው እና ደህና ብር ከኔ ቤተሰቦች ተበድሬ አብረን እንድንሰራ ሀሳብ አቀረበልኝ ። so my question is ንግድ ፈቃድ ምናምን እንዳለ በሱ ስም ነው ያለው ፣በምን አይነት system ነው እኔ የቤቱ 50%ሼር ሊኖረኝ የሚችለው ? በኋላስ ትርፍ እንዴት ነው መካፈል የምንችለው? ፣ በወር ነው ወይስ በአመት ? በዚህ ዙሪያ እውቀቱ ያላችሁ መልሱልኝ ወይም ስለ እዚህ ሀሳብ መረጃ የማገኝበትን ቦታ ጠቁሙኝ
Jun 26, 2025ንግድ ፍቃድ በእሱ ስም መሆኑ ምንም ችግር አያማጣም እንደውም ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት ነው ከዛ ባለፈ ግን የተለያዩ የስራ እቃዎች እና የመንቀሳቀሻ ሂሳብ ለተለያዩ ወጪዎች የሚውሉ ሂሳቦችን ቁጭ ብላቹ በመነጋጋር የስራ ውል በመፈራረም ስራውን መጀመር እዚህ ጋር መጀመሪያ ግን ስራው እና በዛ አከባቢዎች አዋጭ መሆኑን መገንዘብ እና ማወቅ በተጨማሪ ደግሞ ወጪዎች እና ገቢዎችን በየቀኑ ትራንዛክሽን መስራት አለባችሁ...
Jun 27, 2025