ሰላም ለሁላችሁም, ቃላት ና ቋንቋ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያላችሁ እስቲ ይሄንን ጥያቄ መልሱልኝ, ፈሪሳዊ ፡ ማለት ምን ማለት ነው ? [ታሪክ ነክ ና መጽሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች በጥብቅ የተፈቀዱ ናቸው 😊 አመሰግናለሁ,
Jun 25, 2025የማቴዎስ ወንጌልንም ሆነ ሌሎቹን ሶስት ወንጌላት ስታነቡ ወንጌሉ ላይ ተደጋግመው የሚነሱ ሶስት አካላት አሉ ፈሪሳውያን ፣ ሰዱቃውያን እና ጻፎች ምንድናቸው ? የሚለውን በአጭሩ :- 1) ፈሪሳውያን :- ከአይሁድ የሃይማኖት ወገኖች አንዱ ክፍል " እነርሱም የሙሴን ሕግ በብዙ ጥንቃቄ ተረጎሙ። ሰዎች ሕጉን እንዳይተላለፉ ብዙ ትእዛዝና ሥርዓት ጨመሩበት"ይህም ለተራው ሕዝብ ከባድ ሸክም ሆነ (ማቴ15 :1- 4 ፣ 23:1—4)። ዋና አሳባቸው ሰው የሚጸድቀው በግል ሕይወቱና ሕግን በመፈጸም ነው የሚል ነበር (የሐዋ15:5) በመካከላቸው እንደነ ኒቆዲሞስና እንደነ ጳውሎስ ያሉ ቅን ሰዎች ነበሩ ብዙዎች ግን በሕግ ላይ የተጨመረውን የአባቶች ወግ እየተ መለከቱ ዋናውን የሕግ መንፈስ ፍርድን፣ ምሕረትን ፣ታማኝነትንም ረሱ ። በዚህ ምክንያት ክርስቶስ ደጋግሞ ግብዞች በማለት ወቀሳቸው( ሉቃ 11:37- 44 ፣ ማቴ 23)" በክርስቶስ ጊዜ ፈሪሳውያን ስድስት ሺህ ያህሉ ነበር ፤ ሀብታሞችም ነበሩ ፤ ብዙ ጊዜም በምኵራቦች መሪዎች ነበሩ ። ፈሪሳውያንን የተቃወሙ በቤተ መቅደስም ሥል ጣን ያገኙ ሰዱቃውያን ነበሩ (የሐዋ 23 ፡ 6-8)። ፈሪሳውያን ክርስቶስን ለመግደል ተማከሩ (ዮሐ 11: 47-57) » በኋላም አንዳንዶች በክርስቶስ አመኑ (ሐዋ 15:5) ። 2) ሰዱቃውያን :- ክርስቶስ በምድር በነበረበት ጊዜ ከአይሁድ ወገን አንድ ክፍል። ብዙዎች ካህናት ነበሩ ብዙ ጊዜ ሊቀ ካህናት ከእነርሱ ይመረጥ ነበር ከአይሁድ ሸንጎም የሚበዙት ሰዱቃውያን ነበሩ ፈሪሳውያንን በመቃወም የሙሴን ሕግ እንጂ ተጨማሪውን ወግ አይቀበሉም ነበር። ዋና ተስፋቸው በቤተ መቅደስና በሥርዓቱ ነበር በትንሣኤ ፣ በመናፍስት ፣ በሚመጣውም ዓለም ሰው እንደ ሥራው ዋጋውን በመቀበሉ አያምኑም ነበር (ማቴ. 22:23-33 ፣የሐዋ 23:8) ።ክርስቶስ ስለ ሰዱቃውያን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶአል (ማቴ 16: 6-12)። እነርሱም ክርስቶስን አሳልፈው ሰጡት ፣ በኋላም ሐዋርያትን አሳደዱ(የሐዋ 4 ፣1-22)። 3) ጻፎች (ጻፊ) :- በነገሥታት ዘመን በቤተ መንግሥት አገልጋዮችና አማካሪዎች ሆኑ (1 ዜና 27 ፥ 32) ጥሩ ልብስ ለብሰው የቀለም ቀንድ በወገባቸው ይይዙ ነበር (ሕዝ 9፥2) " ከምርኮ በኋላ እንደ ዕዝራ የሕግ ምሁራን ሆኑ (ዕዝ. 7 ፥ 6) በመጀመሪያ ካህናት ነበሩ ' በኋላም ለብ ቻቸው ልዩ ቡድን ሆኑ በደንባቸው መሠረት ለዕለት ኑሮአቸው አስፈላጊውን ነገር በእጅ ሥራ እያገኙ በነጻ ሕግን ያስተምሩ ነበር ፤ ጳውሎስ በዚህ ዓይነት ሥራ እየተጠቀመ ወንጌልን ይሰብክ ነበር (ሐዋ 20:34)። የጻፊ ሥራ ሦስት ዓይነት ነበረ ፤ ይኸውም የሙሴን ሕግ በትክክል መተርጐም (ማር 7:1 --13) ፣ ለሰዎች ሕግን ማስተማር (ሉቃ 22:46) ፣ ዳኛ መሆን (ሉቃ22፡ 66) ነበር ሕጉ እንዳይጣስ የሽማግሌዎች ወግ የተባለውን ልማድ አወጡ። ይህንም በሕዝብ ጫንቃ ላይ ጫኑት (ማቴ.15፡ 2-6) ። ክርስቶስ ስለ ግብዝነታቸው ብዙ ጊዜ ወቀሳቸው (ማቴ 23፣ ሉቃ 20:46-47) ። ከጻፎች ብዙዎቹ የፈሪሳውያንን አሳብ ያጋፊዎች ነበሩ (ሐዋ 23:9)። ጻፎች ክርስቶስንና ሐዋርያትን ተቃወሙ (ማቴ 26:57 ፣ሐዋ 4 : 1-5)። ( ምንጭ :- የኢ.መ.ቅ.ማ.መ.ቃ )
Jun 25, 2025