👉ኢራን የአረብ ሀገር አይደለችም ነገር ግን በብዛት ፋርሳውያን ናቸው 👉እስራኤል የክርስቲያን ሀገር አይደለችም ነገር ግን በብዛት የአይሁድ ነች 👉ሁለቱም ክርስትና እና እስልምና በእስራኤል ውስጥ አናሳ ሃይማኖቶች ናቸው። 👉በእስራኤል ውስጥ ከክርስቲያኖች የበለጠ ቁጥር ያላቸው አረቦች አሉ። 👉በኢራን ውስጥ ከእስራኤል የበለጠ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያኖች አሉ። 👉በእስራኤል ውስጥ ከክርስቲያኖች ቁጥር የበለጠ ብዙ ሙስሊሞች አሉ። 👉ክርስትናን በእስራኤል ውስጥ መስበክ ከባድ ነው ለምነቱም ጥላቻ አላቸው እስራኤልን የምትደግፉበት ምክንያት እስራኤል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለች ወይም የክርስቲያን አገር መስሎን ከሆነ፣ ኢራንን የምትደግፍበት ብቸኛ ምክንያት አረቦች ናቸው ብለህ በማሰብ ወይም በአብዛኛው ሙስሊሞች በመሆናቸው ብቻ ከሆነ ድጋፋችን በፍትህ ላይ ያልተመሰረተ ፣ ህግን በመጣስ ፣ በሰበአዊነት ሳይሆን ላይ ሳይሆን በስሜተዊነት በጭፍን ጥላቻ ነው የሚሆነው
Jun 15, 2025በሰብዓዊነት ሚቃወም እንጂ ሚደገፍ ጦርነት የለም እረፍ። ሲቀጥል ብዙ ጂል ህዝብ ጦርነት ፖለቲካ ሁኖ ሳለ ለራሱ ደስታ ሲል ከሀይማኖት ጋር አገናኝቶ ተመስገን ማሻላ እያለ ያሸረጉዳል። የራሳችን ሚሞተውን እኮ አንድ ቀን አይተን ሳናቅ ነው ቀይ ባህርን አቋርጠን አይናችን ቀይ እስኪሆን በማያገባን ምንፈተፍተው። ለነገሩ በፊልም እያለቀስን ምኑ ያስገርማል ለዚህ እንዲ ደነዝ መሆናችን። to the peoples who have mind እናንተ እዚህ ተመስገን ፍልስጤም ተመታች ማሻላህ አላህ እስራኤሌን ያጠፋታል እያላቹ ምትቀበጣጥሩ፤ እዛ ያለው ሌላ ነው። እዛ ራሳቸው እስራኤላውያን ለማፍጠሪያ ብለው ለአንዳንድ ቦታ ፍልስጤሞች ምግብ ይሰጡ ነበር፣ እዛ ድሮ ሂትለር አይሁድን ሲያሳድድ ፍልስጤም ሸሽጋ ይዛቸው ነበር። እና እባካችሁ አጉል ሀይማኖቱን ማወቅ ሳይሆን መኖርን ልመዱ። ወይ እናንተ እንደምትሉት የሰውን ምኞት ሰምቶ ሚያጠፋ እግዚአበሔር እና አላህ ከመጣም አስረዱን እና እንለያቹ። የዚን ሀገር ጦርነት ተውትና በረሀ ልጆቹን ለማብላት ብሎ በቃጠሎ ሚነዳ ሹፌር ዘሩ ታይቶ ሚገደልበት ሀገር ነው ያላቹት። ቤታቹህ ሳይገባ ቆም ብላቹህ አስቡ።
Jun 15, 2025