እንዴት ናችው? ከባለቤቴ ጋር ከተዋወቅን 7 አመት ሆኖናል በትዳር ሁለት አመት በጓደኝነት 5 አመት እሱ የሚኖረው USA ነው የተዋወቅን ኢትዮጵያ ለረፍት በመጣ ሰአት ነበር ከዛ ተመልሶ ከሄደ በኋላ ለ 5 አመት አልመጣም ነበር ግን ሁሌ እንድጠብቀው ይነግረኝ ነበር ጠበኩት መጣ እና ተጋባን 5ወር ቆይቶ ተመለሰ ልጅ መውለድ ፈልገን ግን አልተሳካም መውለድ በጣም ነው የምፈልገው እሱም እንደዛው አሁን ከሄደ 2አመት ሆኖታል ዜግነት ስለሌለው መምጣት ፈርቷል ዜግነቱን ሞክሮ ግን አልተሳካለትም በተፈጥሮው ቶሎ ነገሮች ላይ ተስፋ የሚቆርጥ እና ያሰበው ካልተሳካ ከዛ በኋላ ወደፊት መራመድ ይከብደዋል በቋንቋ ምክንያት ማለፍ ይከብደዋል ወደፊትም ቢሞክር እና መለያየት እንዳለብን እና የኔን እድሜ ማባከን እንደማይፈልግ ነገረኝ እኔ ደግሞ 1ኛ እወደዋለሁ 2ኛ ሁሉን ነገር አምኜበት እስካገባሁት በችግሩም አብሬው መሆን አለብኝ አሁን ያሳሰበኝ ነገር እድሜየ 31 ነው ቤታችን እኔ እና 1ወንድም ነው ያለኝ እና እኔ እንድወልድ ይፈልጋሉ እድሜዬ እየሄደ ነው በዛ ላይ የቤተሰብ ጫና አለ ለነሱ ምን መልስ እንደምሰጥ አላቅም በጣም ግራ ገብቶኛ የምር ጭንቀት ውስጥ ነኝ የሆነ ነገር በሉኝ ያልታየኝን አሳዬኝ።አመሰግናለው
Jun 15, 2025ሲመስለኝ የትዳር ምንነት አልገባንም ! ! ትዳር ከአሜሪካዊ ዜግነት በላይ ነው ! ትዳር በጋራ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት የሚገቡባት መንገድ እንጂ አሜሪካ የሚገቡባት ሕይወት አይደለችም ! ትዳር ሃገርን የሚገነቡባት ራሷን የቻለች ሃገር ናት ! የእድሜሽ መሄድ ካሳሰበው ከአንቺ ጋር መለያየት እና የገነባውን ትዳር የሚባልን ሃገር መተው ሳይኾን ማሰብ መቻል ያለበት አሜሪካን የምትባለዋን የጦስ ሃገር መተው መቻል ነው የሚኖርበት። እሱ ምቾቱን ፈልጎ አሜሪካን መልቀቅ ከከበደው ትዳሩን መልቀቁ እንዴት ሊቀለው እንደቻለ ሳስበው ( ያስኮንነኝ ይኾን እንጃ እንጂ አሜሪካ ሌላ ትዳር ላለመመስረቱም እርግጠኛ አይደለኹም ) እስከማውቀው ድረስ ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እምመንበሩ ነው ሰማያዊውን ወልደ እግዚአብሔር በምድር ያመላለሰ ፍቅር ነው እንኳን ያቺን በሽቃጣ አሜሪካንን አይደለም ምንንም ያስተዋል። አንቺ ግን እውነት ፍላጎትሽ ልጅ ብቻ ነው ? ትዳርሽ ተመችቶሻል ?
Jun 15, 2025