ሰላም ወገን; Urgent fin tech investment byd መኪና እያስመጣ ይሸጣል ይባላል።ትክክለኛ ነው ወይስ እንደሌሎቹ ዘርፈው ይጠፋሉ?
Jun 14, 2025መዝረፉ ምናምን እንዳለ ሆኖ ... ከዛ በፊት ኤሌክትሪክ መኪኖችን ስትገዛ ምን ማሰብ አለብኝ ብለህ ጠይቅ... እኔ አውቶ ኢንደስትሪውን በጥልቅ ስለማላርፍ እንዲህ እንዲያ እያልኩ ማቡካካት አልሻም (በአደባባይ) በግል ቢሆን የራሴ ምልከታዎች አሉኝ እንደ አንድ ኤሌክትሮኒክስ ቴክኒሻን.. ስለዚህ ቀድመህ መጠየቅ ያለብህ የነዳጅ መኪና ወይስ የኤሌክትሪክ ብለህ ብቁ በዘርፉ ያሉትን መጠየቅ አለብህ... እንዳልኩህ በአውቶሞቲቩ ጥልቅ እውቀት ባይኖረኝም .. የኤሌክትሪክ መኪኖች ግን ሀገራችን ላይ ቢያንስ 4 አመት መሞከር አለባቸው ባይ ነኝ... በተለይ BYD ቅርብ አመት የመጣ ስለሆነ መጪው ወጪ ከስፔርፖርት አንፃር አይታወቅም... ምሳሌ እንኳን BYD ቴስላ ራሱ ብዙ እንከን እየገጠመው ነው ከኢንቫይሮመንት አንፃር.. ስለዚህ ስትወስን መኪናው በእጅህ መግባቱ እንዳለ ሆኖ ሚያስጨንቅህ... ተጠቅሜበትስ ልሽጥ ብል ትርፋማነቱ ምን ያህል ነው ሚለውን ማገናዘብ ግድ ነው... ምክንያቱም እስካሁን ባለው እውነታ አንድ የነዳጅ መኪና እና አንድ ኤሌክትሪክ መኪና እኩል የገዙ ግለሰቦች ከ7 ወርበኃላ ሊሸጡት ቢያስቡ [የነዳጁ ቢያንስ ከ30-45% ከገዛበት በላይ ይሸጣል... የኤሌክትሪኩ ግን ከገዛበት በትንሹ 15% ወርዶ ነው ሚሸጠው] ምክንያቱም ባትሪው ይወርዳል ላይፍ ታይሙ
Jun 14, 2025