ሰላም ቤተሰብ ገቢዬ በወር 20ሺ ነው ከቤት ለመውጣት እያሰብኩ ነው እና ሚበቃይ ይመስላችሀል እና ቤት እስከስንት አገኛአለው
Jun 10, 2025አዎ ትችላለህ። አሪፍ ሀሳብ ነው። ግን ቤት ኪራይ እና ትራንስፖርት ከግማሽ በላይ ገቢህን እንደሚወስሩት ማወቅ አለብህ (ቅርብ ቦታ ብትከራይ፣ ትራንስፖርት ትንሽ ቢሆንም ቤት ኪራይ ግን ውድ ነው። ሩቅ ቦታ ሲሆን ደግሞ ቤት ኪራዩ ቀንሶ ትራንስፖርቱ የዛኑ ያህል ይጨምራል) በቀረችው ግማሽ ገቢህ ራስህን ማስተዳደር አያቅትህም ግን On a budget ነው የምትኖረው። ታክሲ ቢረፍድብህ Ride መጥራት፣ ከጉደኞችህ ጋር ወጣ ብሎ መዝናናት፣ ስልክ መቀየር የመሳሰሉት ነገሮች ቅንጦት ይሆኑብሀል። ከዛም በላይ ደግሞ ለEmergency የሚሆን ገንዘብ save ለማድረግ ሊከብድህ ይችላል። እንደኔ ሀሳብ, ከቤተሰብህ ጋር መኖር የምትችል ከሆነ እና እድሜህም ገና ከሆነ... ከነሱ ጋር እየኖርክ ትንሽ ገንዘብ ያዝ። የወር ገቢህንም አሳድግ። በዚ ኑሮ ውድነት የቤት ኪራይን ወጪ አለማሰብ ራሱ ትልቅ opportunity ነው።
Jun 10, 2025