For ORTHODOX only Tselot metseley sfelg endesra endalasbew weym endehone gdaj endalasbew miyaregegn hule endezi sisemagn anbbew mberetatabetna le tselot fkr endinoregn miyaregegn ater yale tsuf tsafulgn. 🙏🙏🙏 😇
Jun 07, 2025ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እና እርዳታውን መጠየቅ ማለት ነው። እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ እንድትወደው ስለምትፈልገው ጉዳይ ከእርሱ ጋር ተነጋገር። የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ መጽሐፍ ቅዱስን እና ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎችን በማንበብ እግዚአብሔርን የበለጠ ማወቅ ትችላለህ። ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ያለህን ግንኙነት ያጠናክራል። በጸጥታ ጊዜ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ፍቅሩ ማሰብ። ይህ በውስጥህ ያለውን ሰላም እና እምነት ያሳድጋል። በእግዚአብሔር ስራዎች ላይ ስታተኩር በህይወትህ ውስጥ እግዚአብሔር ያደረጋቸውን መልካም ነገሮች አስታውሰሰ። ይህ ለእርሱ ያለህን ምስጋና እና ፍቅር ያሳድጋል። በጸሎት እና በትዕግስት እምነትህን ማሳደግ ትችላለህ። ቅዱስ ዳዊት “ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ እንዲሁ ነፍሴ አንተን ተጠማች” እንዳለው እግዚአብሔርን የመጠማታችንን ልኬት ለመጸለይ ባለን ጉጉት እናውቀዋለን። ለምሳሌ ያክል የምንወዳቸውን ስናስብ ምን ይሰማናል? የሚናፍቁንን ሰዎች በስልክ ስናወራስ ደስታችን ምን ያህል ነው? በእውነቱ እነሱን ለማውራት በቀን የስንት ብር የሞባይል ካርድ እንሞላ ይሆን? ምንስ ያህል ሰዓት ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እናወራለን? ያም ብቻ አይደለም እንዲህ የናፈቅነውን ሰው በአካል ስናገኝውስ ምን ያህል ደስ ይለናል? እግዚአብሔር እኛን በየዕለቱ ሊያዋራን ይፈልጋል:: እርሱ በየደቂቃው ሳይሰለች ያንኳኳል አስቡት እስኪ በደንብ! ሁሉን የሚያውቅ አምላክ ነው በዛ ላይ እኛ ምን ያህል ክፉዎችና በደለኞች እንደሆንን እያወቀ እንኳን ሊያናግረን ይፈልጋል፡፡ ሌላኛው እና ወሳኙ ነገር አቅምን መለየት ነው እንደ ጊዜያችን እና እንዳለንበት ሁኔታ አንጻር ቀስ በቀስ ልናድግ ምንችልበትን ጸሎት መጸለይ ነው መንፈሳዊ ህይወት ስንጀምር እንደ ፍፁማን ለመሆን መጣር አይገባም። ይኽውም በአንድ ቀን መቶ ሃምሳ መዝሙረ ዳዊት መድገም የሰባቱንም ዕለታት ውዳሴ ማርያም መድገም በአንድ ቀን እስከ 12ሰዓት መጾም ፤በአንዴ በሁሉም አገልግሎቶች ላይ ለመሳተፍ መሞከር ወዘተ... ካቅም በላይ መጉረስ መታነቅን ያመጣል ነገር ግን ቀስ በቀስ ማደግ/ማሳደግ ይገባል። " ጀማሪ ክርስቲያን ....." እንደሚባለው እንዳይሆን በነገሮች እርጋታና ማስተዋል ያስፈልጋል። ያለበለዚያ ዝለትን ያስከትላል።በየጥቂቱ በመንፈሳዊ ሕይወት ማደግ ከዝለት ይጠብቃል። እዲሁም ምክኒያቶቻችንን ሁሉ ዛሬ ላይ ልንገድላቸው ይገባል ዛሬ ላይ ካልገደልናቸው እነርሱ ነገ ይገድሉናል ።
Jun 07, 2025