Selam endet nachu ልመረቅ 1wer new ykergh ena ተቀጥሬ ከምሰራ የራሴን ስራ በትሹ ልጀምር ብዬ ብር ብድር እንኳን ለመጠየቅ ሳስብ ቤተሰቦቼ ቅስሜን ስብር ነው የሚያደርጉት ማበረታታት የሚባል ነገር አያውቁም አንቺ ብለው ይስቁብኛል አንቺ አትሆኚም ይሉኛል በቃ አልቻልኩም በተናገሩኝ ቁጥር እንዴት እንባ እንደሚተናነቀኝ እነሱ ፊት ላለማልቀስ የማደርገው ጥረት እንዴት ልግለፅላችሁ እና እስኪ አግዙኝ ከ 0 ተነስቼ ምን አይነት ስራ ልስራ ? እስኪ በዚህ ሁኔታ ያለፋችሁ አግዙኝ
Jun 06, 2025ጣት አትቀስራ መጀመሪያ ምን እንደምትሰሪ እወቂ እዛ ስራ ላይ እውቀት እና እምነት ሲኖርሽ እነሱን እራሱ ማማከር ሳይጠበቅብሽ መበደር ትችያለሽ ምክንያቱም ሀላፊነት ነው የሰው ገንዘብ ቀላል ነገር አይደለም ነብስ ሊያስከፍል ይችላል መጀመሪያ ምትሰሪውን እወቂ ከዛ ለይ ይሄ ነገር ያዋጣል አያዋጣም ሚለውን አጥኚ እነሱም ትክክል ናቸው ገና ምትሰሪውን ሳታውቂ ብሩን አምጥተሽ እዚም እዛም ልታደርጊው ነው? ከዛ ምን ሊውጥሽ ነው ለዛ በመጀመሪያ እርግጠኛ ሁኚ ምንም አይነት ስራ ይሁን መጀመሪያ ከኔ ጋር ይሄዳል ለኔ ይስማማል ወይ ንግድ ከሆነ ከሰው ጋር ተግባቢ ነኝ ወይ ብለሽ ጠይቂ ከዛም ደንበኛ አያያዝ እንዴት ነኝ ብለሽ ለ 3 ወር ሱፐርማርኬት የሆነ ሰው መሀከለኛ ሚበዛበት ሱቅ ተቀጠሪ ሴት ስለሆንሽ ደንበኛ የመሳብ access አለሽ እንዲ ነው እንጂ ሚሰራው ምትሰሪው ነገር ላይ ምንም እወቀት ሳይኖርሽ ብር በነፃ ቢሰጥሽ ራሱ ትርፉ ኪሳራ ነው በተረፈ አትጨናነቂ ግን ጊዜ ውሰጂ ከቀን ቀን ጥሩ ጥሩ የሚሻሻሉ ሀሳቦች ይመነጫሉ🤗
Jun 06, 2025