ዛሬ ask anything ከተከፈተ 6ተኛ አመቱ ነው🎈🎈🎈🎈🎁🎁 እስኪ ትንሽ እንደ anniversary -ያሳቃቹ ጥያቄ -በጣም የጠቀማቹ መልስ ወይንም ጥያቄ -እዚህ ቻናል ይቅር ምትሉትን -ተጨማሪ ይደረግ ምትሉትን በቅደም ተከተል እንደ ጥያቄው መልስ ስጡልን🤩🤩
Jun 05, 2025እውነቱን ለመናገር ይሄን ቻናል የተቀላቀልኩት ...በጣም ብቸኝነት ይሰማኝ እና ሁሉም ነገር ጨላልሞብኝ በነበረ ወቅት ነበረ። የውስጤን ጩኸት ላለማዳመጥ ስል እዚህ እየመጣሁ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ማንበብ እና መመለስ ይገባኛል ብዬ የማምናቸውን ደግሞ ረዘም እና ዘለግ ያሉ መልሶችን በመፃፍ ውስጥ ...ከውስጤ ጩኸት እና ህመም መደበቂያ ሆኖልኛል! ከአስቂኝ እስከ አሳዛኝ ከጠቅላላ ዕውቀት እስከ የሚያስቁ ጥያቄዎች ...እዚህ ብዙ አይቻለሁ ብዙ አንብቤያለሁ ብዙም ተምሬያለሁ! ደስ የሚል ማህበረሰብ ነው ... በዚህ አጋጣሚ የአንድ ሰው ህይወትን አድኜበታለሁ ይሄን ቻናል ...ራሷን ለማጥፋት ከጫፍ ደርሳ የነበረችን እህታችንን በዚሁ platform አግኜቻት ብዙ አውርተን በብዙ ልመና በብዙ እንባና ልመና ቆይታልኝ ዛሬ በህይወት ያለች ደስተኛ እና ፍልቅልቅ የልብ ወዳጅ አግኝቼበታለሁ! Ask anything ለኔ ...ትቶ የማይተወኝ ወዳጄ ነው! ሁላችሁንም እወዳችኋለው ሁላችሁንም አመሰግናችኋለው! ተሳዳቢዎች እና ሃይማኖታዊ ክርክር በማንሳት ልታበጣብጡን የምትሞክሩም ጭምር ...እንወዳችኋለን ብቻ አታበጣብጡን! አድጎ ተመንድጎ ለ 10፣ 20፣...ለ50ኛ ዓመት ጊዜ ሳይለየን ከቁጥር ሳንጎድል ለዚያ ያብቃን። 🙏
Jun 05, 2025