Selam AAE family, አሁን ላይ በጣም ግራ ገብቶኛል እባካችሁ አማክሩኝ ከዚ ሰው ጋር የተገናኘነው እሱ የብሬክስሩ ገለፃ ሊሰጠኝ ስልኬን ሲቀበለኝ ነው 8ወር በግኑኝነት ቆይተናል መጀመሪያ ላይ በጣም ጥሩ ግንኙነት ነበረን ከዛ ግን እየቀየሰ ጭራሽ ሊጠፋ ነው ጥሩ እና መጥፎውን ልንገራቹ ጥሩ፣ በጣም ትዕግስተኛ ነው ተጫዋች ነው ለመለወጥ ይታትራል ወንዳወንድ ነገር ነው ጥሩ ያልሆኑት፣ የፍቅር ቃላት የፍቅር ጨዋታ አይችልም ሁሌ እኔ ነኝ እሱ ጋር እንድሄድ ሚፈልገው(እሱ ያለበት ወደስራ መንገዴ ላይ ነው ቢሆንም ግን... ) ስልክ ስደውል አብዛኛውን ጊዜ ተይዟል አሁን አሁን ደሞ አይቶትም ዝም ይላል ሳይደውል ቀናት ያልፋሉ ስጠይቀው ስራ በዝቶብኝ ይላል አንድም ቀን አበባ ወይ ምንም ሰጥቶኝ አያውቅም (ምን ያህል እንደምወድ ያውቃል ) ለልደቴ እንኳን ምንም የለም ከቤተሰቡ ጋር ነው ሚኖረው 12 አመት ይበልጠኛል እንደዛም ሆኖ ብድር ይጠይቀኛል ይበቃናል ብዬ ላቋርጥ ስሞክር አስተካክላለሁ የኔ ጥፋት ነው ይቅርታ አርጊልኝ ይላል ሆኖም አልተስተካከለም ምን ይሻለኛል
Jun 05, 2025አረ ሴቶች ግን እሄን ሁላ ምልክት እያያቹህ እንዲት ነው አብራቹህ ምትሆኑት በቃ አሁን በፍቅር ላ ሆናቹህ እንዲህ ከሆነ አስቡት እሄ ነፈ ትዳር ስትይዙ ስለዚህ በጊዜ አምልጭ
Jun 05, 2025