ሰላም ሰዎች እንዴት ናችሁ am 24 እናም ዲያቆን ነኝ እጮኛ ነበረችኝ ለ 3 አመታት እናም በጣም ወዳታለው እሳሳላታለሁም ያው በተክሊል ለመጋባት ስለምናስብ ምንም የለንም ተሳስመን እንኳን አናውቅም ለሶስት አመታት በጣም ቆንጆ ነች ጨዋ ነች ሀይማኖቷ ላይ በጣም ጠንካራ ነች ግን 1. እሷ በጣም የሀብታም ልጅ ነች እኔ ደግሞ በጣም የድሀ ልጅ ነኝ ያላባት ነው ያደኩት ምናምን ያው አባቴ በአንድ አመቴ ነው የሞተው ምናምን እና እናቴ በስቃይ ነው ያሳደገችኝ። እና የሷ ቤተሰቦች ከኔ ጋ እንደሆነች ቢያቁ ክብራቸው እንደተነካ ነው ሚቆጥሩት። 2. በጣም እፈራለው ሰው ከኔ ጋር እንዳያያት እና በጣም ዋጋ እየከፈለችልኝ ነው በጣም ተጎዳች ለኔ ብላ even ከቅዳሴ ስንመለስ እንኳን አብሬአት ሰው ሲያየኝ በጣም ነው የማፍረው የምሳቀቀው ለምንድን ነው🤔 3. ሚስቴ ብትሆን ደስ ይለኛል ግን የሚሆን አይመስለኝም ሰዎች ምን ትመክሩኛላችሁ ልተዋት እልና አቅም አጣለው አብሬአት ብሆን ደግሞ በርግጠኝነት ከቤተሰቦቿ ጋር ትጋጫለች ጨነቀኝ ደግሞ ከሷ ውጪ ወድጄ አላውቅም አና በጣም ነው ምወዳትደ ምንድን ነው ምትመክሩኝ በማርያም ጨነቀኝ
May 31, 2025ዋናው እራስህን መለወጥ መቻልህ ነው እራስህን በትምህርት እና በምግባር ተሽለህ ከተገኘህ በራሱ ሀብት ነው....በተረፈው ለሚፈጠረው ነገር ሁሉ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ሁን...ነገ የእራስህን እና የእናትህን ታሪክ መቀየር ብትችልም ከሚወደህ እና ከምትወደው ሰው ጋር ካልሆንኩ ህይወት መሉ አትሁንም....
May 31, 2025