ሰላም ቤተሰቦች እንዴት ናቹህ የኔ ጥያቄ በእድሜ ቢያንስ ከ25 በላይ ለሆኑ ወንዶች ነው ፤ አንድ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ 2ኛ አመት ተማሪ አንዲትን ከሱ በእድሜ በ1 አመት የምታንስን ነገርግን በBatch እኩል የሆነችውን ሴት ቢወዳት እሷም ብትወደው እና Passionቻቸው ማለትም ወደፊት መስራት የሚፈልጉት ስራ ተመሳሳይ ቢሆን ፣ ሁለቱም በሃይማኖታቸው ጠንካራ Orthodox ቢሆኑ ነገር ግን የመጡበት ቦታ እሱ ከአማራ ክልል እሷ ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል ብትሆን (እዚህ ላይ ማወቅ ያለባቹ ሁለቱም በጣም ጠንካራ ፣ ታታሪ እና ጎበዝ ናቸው ትምርት ላይም ስራ ላይም እና ተነጋግረው ሁለቱም መኖር የሚፈልጉት እዛው አርባምንጭ ቢሆን እንዴት ነው ግንኙነታቸውን ማጠናከርና ለወደፊት ምናልባት ከተመረቁ በኋላ ሊፈጠር የሚችል መለያየትን ማጥፋት የሚችሉት ... እዚህጋ መቼም ከወንዱ በርግጠኝነት የሚጠበቅ ነገር ይኖራል እና ከሷም ሚጠበቅ ነገር ይኖራል ... እና ጥያቄዬ በዚሁ ግንኙነታቸው እስከ ምርቃትና ከምርቃትም በኋላ ለመቀጠል ምን ማድረግ አለባቸው ... እንዳልኳቹህ ምክር የምፈልገው በዚህ ህይወት ካለፈና ጠንካራ ከሆነ ሰው የሚሰጥ ሀይማኖታዊና አለማዊውንም የያዘ ምክር ነው ...(ከተቻለ Positive ምክር ቢሆን ደስ ይለኛል) አመሰግናለሁ 🙌🏻
May 30, 2025የዘር መለያየት ምንም ነው የእድሜ መበላለጥም እንደዛው እውነተኛ ፍቅር ካላችሁ እና መተሳሰብ የምትችሉ ከሆነ ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ ውጤታማ ትሆናላችሁ እመነኝ
May 30, 2025