መጀመርያ ኦርቶዶክስ የነበራቹ አሁን ደሞ ፕሮቴስታንት የሆናቹ ለምን እንደቀየራቹ ምክንያታቹን ንገሩን እስኪ
May 27, 2025ለስእላት መስገድ-የጣኦታዊነት ታናሽ ወንድም ጥንታዊያን ክርስቲያኖች የስደታቸው አንዱ ምክንያት “አልቦ አማልክት” (Atheists) ናቸው የሚል ሲሆን ከሳሾቻቸው ይህንን ያሉበት ምክንያት በክርስቲያኖቹ ፊት የሚሰገድለት ምንም ቁስ ባለመኖሩ ነበር። ኦርቶዶክስ ወገኖቻችን ደግሞ ትምህርትና ልምምዳቸው ከአባቶች የተቀዳ ለመሆኑ ብዙ ሲከራከሩ ይስተዋላል። እውነታው ግን ቤተክርስቲያኒቱ የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን የምትመስለው በተወሰኑ ስርአታዊ ጉዳዮችና ጥቂት ትምህርቶች ላይ ብቻ ነው እንጂ ከጊዜ በኋላ ገብተው የተከማቹ ሐሳዌ ትምሕርትና ልምምዶች በሙላት ይገኙባታል። ይህንን ለመመልከት በስእል ፊት የመስገድ እሳቤያቸውን እንደ ምሳሌ እናንሳ። በቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት መሰረት በስእል ፊት መስገድ ከባለ ሰሉ በረከትና ረድኤትን መለመን ነው፤ ከዚህም ባለፈ የቤተክርስቲያን ህልውና ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ልምምድ እንደሆነ ሊቃውንቱ ይናገራሉ፤ ያው የደረቀ ነጭ ውሸት ቢሆንም ማለት ነው። ለስእል መስገድ እንኳን በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ቀርቶ በ4ኛው ክ/ዘ እንኳን ቢኖር ትልቅ ተቃውሞ ነበር የሚገጥመው። እስቲ ከ4ኛው ክ/ዘ ኤጲፋንዮስ ሰላሚስ የተባለውን አባት እናንሳ። ይህ አባት በአንድ ደብዳቤው በአንድ ስፍራ የነበሩ ክርስቲያኖች መጋረጃቸውን ስለቀደደባቸው እንዳዘኑበት ይናገራል፤ መጋረጃውን የቀደደበትን ምክንያት ደግሞ እንዲህ ይተርካል፤ “አናብላታ በምትባል መንደር እያለፈሁ ሳለ በዚያ መብራት ሲበራ ተመለከትኩ። ቦታው ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ጠይቄ ስለተረዳሁ በዚያ ለመጸለይ ገባሁ፣ እናም በዚያ ቤተ ክርስቲያን በሮች ላይ የተንጠለጠለ የቀለመና ጥልፍ የተጠለፈበት መጋረጃ አገኘሁ። ምስሉ የማን እንደሆነ በትክክል ባላስታውስም የክርስቶስን ወይም ከቅዱሳን የአንዱን ምስል ይዞ ነበር። ከቅዱሳት መጻህፍት ትምህርት ተቃራኒ በሆነ መልኩ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሰው ምስል በመሰቀሉ ስለተበሳጨሁ (መጋረጃውን) ቀዳድጄ የቦታውን ጠባቂዎች ለድሆች እንደ መግነዝ እንዲጠቀሙበት መከርኳቸው።” [1] በኤጲፋንዮስ ትረካ መሰረት እንኳን ለስእል መስገድ ቀርቶ የቅዱሳንን (የኢየሱስን ጨምሮ) በዚያ መልክ መስራት ውጉዝ ነው። ስለዚህ ቤተክርስቲያኒቱ ኤጲፋንዮስን አትመስልም! እንደዚሁም በ3ኛው ክ/ዘ የኖረው አርጌንስ ክርስቲያኖች የሚሰገድለት አካል ስለሌላቸው ለሚከሳቸውና ሴልሰስ ለተባለው ግሪካዊ ፈላስፋ የሚከተለውን ይመልሳል፡ "ነገር ግን (ሴልሰስ) በመንፈስ የተነሳሱ ለማለት የፈለጋቸው ሰዎች ኦርፊየስ፣ ፓርሚንደስ፣ ኢምፔዶክለስ፣ ወይም ራሱ ሆሜር፣ እና ሄሲዮድ ቢሆኑም የትኛውም ሰው ቢሆን እነዚያ መመሪያቸውን የተከተሉት በእግዚአብሔር ቃል አንድ አምላክ ወደሆነው የቃሉ አባት ይመለከቱ ዘንድ በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ቤት እየተማሩ ምስሎችን እና ሃውልታትን እንዲሁም የአይሁድን አጉል እምነቶች ሁሉ ከካዱት ይልቅ እንዴት በተሻለ መንገድ እንደሚሄዱ ወይም የላቀ ሕይወት እንደሚመሩ ሊያሳየን ይገባል። [2] እንደ አርጌንስ ገለጻ ከሆነ ከኢየሱስ የተማሩ ሁሉ የሚሰገድለትን ግዑዝ አካል የካዱ ናቸው። ስለዚህ ለስእል የሚሰግዱ ሁሉ ከኢየሱስ ባልተማሩት “ብርሃን” እየተመላለሱ ነው። እዛው 3ኛው ክ/ዘ ላይ ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ ደግሞ የጥበብ ስራዎች ሁሉ ቅዱስም መለኮታዊም ሊሆኑ እንደማይችሉ አስረግጦ እንዲህ ይናገራል፡ “በጠቢባን የተሰሩ ምስሎች እና ቤተመቅደሶች ከማይንቀሳቀሱ ነገሮች የተሠሩ ናቸው; ስለዚህ እነርሱ ደግሞ ግዑዝ፣ ቁሳዊ፣ እና ርኩስ ናቸው፤ ….. የጥበብ ስራዎች ቅዱስ እና መለኮታዊ ሊሆኑ አይችሉም።” [3] ከ 3 እስከ 4ኛው ክ/ዘ የኖረው ሌላው ክርስቲያን ጸሃፊ ላክታንቲየስ ደግሞ ጭራሽ በምስሎች ውስጥ ሃይማኖት ሳይሆን ሃይማኖትን ማስመሰል እንዳለ ቁርጥ አድርጎ ይናገራል። “በምስሎች ውስጥ ሃይማኖት የለም፤ ምክንያቱም ከምድር በተሰሩ ነገሮች ምንም ሰማያዊ ነገር ሊኖር አይችልምና። . . . በምስሎች ውስጥ ሃይማኖትን ማስመሰል እንጂ ሃይማኖት የለም።” [4] ቅዱሳን የምንላቸውን ሰዎች ስእል ቀርጾ መስገድ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመናት ፈጽሞ የማይታወቅ የጣኦታዊነት ታናሽ ልምምድ ነው። ያው እኛ ሰፈር “ለስእል ያልሰገደ ከቆመበት ይጥፋ” ተብሎም ተረግመናል። ይህ ታዲያ በመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲኢያን ያልነበረ፤ አባቶች የተቃወሙት በኋላ ዘመናት ስርዋጽ የገባ ባእድ ልምምድ ለመሆኑ ታሪክ ምስክር ነው። እርግጥ ነው ክርስቲያኖች መልእክት ለመለዋወጥም ሆነ ለመማማር ስእላትን ይጠቀማሉ፤ እንደ ጣኦታውያኑ ሰግደውላቸው ግን በፍጹም አያውቁም። ያው ቤተክርስቲያን ልትሳሳት እንደምትችል አንዱ ማሳያችን ነው lol😁 [1] Epiphanius, Letter 51.9) [2]Origen, Contra Celsum book 7: section 41 [3]Clement of Alexandria, Stromata 7.5 [4]Lactantius, Divine Institutes 2.19 https://t.me/hokhmahchristianstudies https://t.me/hokhmahchristianstudies
May 27, 2025