በጣም ይገርማል ጊዜና ሰው ሲጥል ትላንትን አያይም 🤔 ህም በተለይ ሰው በምን ያህል ፍጥነት እንደሚቀየሩ ስንት አመት አብረን አሳልፈን ልባችንን ገመናችንን ደስታችንን ሀዘናችንን የሚጋሩ የምናውቃቸው በጣም የቅርብ ጓደኞቻችን በአንዴ ተቀይረው አጥፊዎቻችን ሲሆኑ ማየት ያማል በጣም የምወደው ባሌ እንዲሆን ከማሰብም በላይ የአብሮነትን መንገድ በጋራ የጀመርነው ፍቅሬ በጣም ከምወዳት የስራም የህይወትም አስተማሪየ የብዙ አመት የልብ ጓደኛየ እህትነቷ ይበልጥብኝ ከነበረው አጠገቤ ካለች ሴት ጋ የፍቅር ግንኙነት እንዳላቸው ከዛም አልፍ አብረው እንዳደሩ ሳውቅ የምር ሰው መሆኔን ጠላሁት ምን እንዳጠፋሁ አላውቅም ፈጣሪስ ምን ሊያረገኝ እንደፈለገ አልገባኝም አለም የተደፋችብኝ ያህል እያፈነኝ ነው በቃ መናገርም ማልቀስም መኖርም አቅቶኛል ስራየንም ቤተሰቦቼንም ተቼ የማደርገውን ነገር አላውቅም እሱን አጊኝቼው የክህደት ትክክለኛ መልስ ባይኖረውም ለምን የሚለውን የውስጤን ጥያቄ ቢመልስልኝ ደስ ይለኛል ግንኙነታችን እንዲቀጥል አልፈልግም የሚያፈቅር ልብ ለካ መጥላትም ይችላል ያፈቀርኩትን ያህል ጠላሁት ግን ደግሞ ከተለያየን ቦሀላ በጣም ይመኘው የነበረውን ልጅ በሆዴ መያዜን አወኩኝ በጣም ግራ ገብቶኛል ምን እንደማደርግ አላውቅም 😪
May 27, 2025Don't 👏 Start 👏 Sexual 👏 Relations 👏 Before 👏 Marriage 👏
May 27, 2025