Hey guys have u ever struggled with bad intrusive thoughts that just don't won't leave u alone and continuesly pops up to your mind and disturb your mental wellness......if that's the case how did you resolve it please I'm struggling to get out of this situation
May 20, 2025ሰላም ለጥያቄው መልስ ለመስጠት ያህል ...አዎ ይሄ በህይወት ውስጥ የሆነ አጋጣሚ ላይ ሁላችንንም ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው! የሃሳቡ አይነት በዝርዝር ስላልተገለፀ ለማብራራት ነገሮችን ከበድ ቢያደርገውም ነገር ግን ከግል ልምዴ በመነሳት ጥቂት ነገር ልበል! አዕምሯችን በአፅናፈ ዓለም ውስጥ ካሉ አስደማሚ ፍጥረታት አንዱ ነው! የኛው ሆኖ እኛው ተሸክመነው እየዞርንም ጭምር 100% መረዳትም ሆነ በሚገባው ልክ መጠቀም አልቻልንም! የመሰል ሃሳቦች ምንጭ የተለያየ ሊሆን ይችላል ...ለምሳሌ በኮምፒተሩ ዓለም የሚታወቅ አባባል እንዋስ "Garbage in Garbage out" ምንም ያህል ኮምፒተሩን የምንመግበው መረጃ ብዙ ቢሆን ትክክለኛ እና አስፈላጊ ካልሆነ ኮምፒተሩ የሚሰጠን ምላሽም የተሳሳተ ነው! በተመሳሳይ ወደ አዕምሯችን ለምናስገባው መረጃ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን! የምናያቸው ፊልሞች፣ የምንከታተላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች፣ የምናነባቸው መፃህፍትና ፅሁፎች ሁሉ በአዕምሯችን ላይ የሚያሳድሩት አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለ ማስታወስ ያስፈልጋል። ስለዚህ ለነኢህ ነገሮች መጠንቀቅ እና ምናልባትም ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልግ ይሆናል ለምሳሌ Action/Horror የሆኑ ፊልሞችን ማዘውተር ቀስ በቀስ የርህራሄ ሰዋዊ ባህርይን እየሸረሸረው እንደሚሄድ ጥናቶች ያሳያሉ። ሌላው ውሏችንን መዳሰስ ነው፤ ውሏችንን እንመስላለን ስለሆነም ጓደኞቻችን በዙሪያችን ያለው አካባቢ ምን ይመስላል የሚለውን መቃኘት እና አስፈላጊ የሆኑ ማስተካከያዎችን ለማድረግ መጣር ያግዛል። ቀደም ሲል ሌሎችም ባነሱት ሃሳብ እስማማለሁ! እኛ ስጋ ብቻ አይደለንም ውስጣችን እውነትን የሚፈልግ አምላክን የሚራብ ማንነት አለን ...የሱን ድምፅ ፀጥ ለማድረግ በሱስ አሊያም በሌሎች መዘናጊያዎች ትኩረታችንን መከፋፈል ትርፉ ህመምና ስቃይ ነው! አምላክን ከልብ መፈለግ ለመንፈሳዊ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት መሞከር አዕምሮን ከመጥፎ ሃሳቦች ለማራቅ የሚረዳ ትልቅ እርምጃ ነው! በሃይማኖት አጥር ከመታጠር ባለፈ ስለ ሌሎች እምነቶችም ለማወቅ ጥረት ማድረግ ጥሩ ነው! ክርስቲያን ከሆኑ መፅሐፍ ቅዱስን አዘውትረው በየለቱ ማንበብ ለውጥ ያመጣል! በቀን 1 የመፅሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ብቻ ማንበብ በራሱ ትልቅ ለውጥ ያመጣል (እኔ ክርስቲያን ስለሆንኩ ነው ስለመፅሐፍ ቅዱስ ያወራሁት)፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሊረሳ የማይገባው ግን ከሰማዩ አባታችን ጋር በፀሎት መነጋገር ነው! ፀሎት የሚደጋገም ድግምት አይደለም፤ አንድ ልጅ ለሚወደው አባቱ ያስደሰተውንም ያሳዘነውንም ሁሉ እንደሚነግረው ሁሉ ለአፍቃሪው እና የእውነት በግለሰብ ደረጃ ስለሁላችንም ለሚያስበው ደግ የሰማዩ አባት የልባችንን ሸክም ሁሉ ለእሱ ማፍሰስ ነው። በነፃነትና በአክብሮት የሚቀርብን ፀሎት አምላክ ይሰማል ደግሞም በሚያስገርሙ መንገዶች ይመልስልናል። እነዚህ እርምጃዎች እኔን በእጅጉ ያግዙኛል! ምናልባት ነገሩ ከተደጋገመና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን እስከማወክ ከደረሰ ግን የህክምና እርዳታ ማድረጉ መልካም ነው ምናልባትም በሳይንሱ መልስ የሚገኝለት የስሜታዊ ቀውስ ወይም የስነልቦና/ስነአዕምሮ እክል ከሆነም መፍትሄ ይበጅለታል! ህይወት ጉዞ ናት ከፍታም ዝቅታም አላት ግን ተስፋ ሳይቆርጡ የተጓዟት ደስተኛ መሆናቸው አይቀርም 🙏
May 21, 2025