ሰዎች ሀሳብ ስጡበት እስኪ ከተመረቁ 2 አመት ሞላኝ ስራ አላገኘውም እና በቅርቡ father ጋር እያወራን ነበር እና የ እኔ ሃላፊነት ማስተማር ነው ሃላፌነቴን ተወጥቼ ጨርሻለሁ አለኝ ከዚህ በኃላ አያገባኝም እንደ ማለት ነው። ከዛ እኔ በጣም ተናገርኩት ግን አሁን በጣም እየደበረኝ ነው በመናገሬ እኔ ጥፋተኛ እሆን? እስኪ ንገሩኝ አስተምሮ ማስመረቅ ነው የቤተሰብ ሀላፊነት? ስራ አለማግኘትስ የኔ ጥፋት ይሆን? እሱ ልክ ይሆን ይቅርታ ብጠይቀው ለዉጥ ይኖረው ይሆን?
May 17, 2025አዎ ጥፋተኛ አንተ ነህ... የቤተሰብ ኃላፊነት አንተን ማስተማር ነው... ከዚህ በላይ ምንም ሊያደርጉ ግዴታ የለባቸውም.... ዞር ዞር ብለህ የተገኘውን እንደመሥራት አባትህን የመናገር ሞራል ካገኘህ ችግሩ ያንተ ነው... ስራ አገኘህ አላገኘህ ያንተ ጉዳይ ነው እንጂ የቤተሰብህ አይደለም.... እነሱም መቼም አይመለከተንም ብለው ከቤት አላስወጡህም እንደቤተሰብ አብረው እያኖሩህ ነው... ምንም ግዴታ የለባቸውም... ይልቅ የሚሻልህ ቤተሰብ እንደሌለው ሰው ኢጎህን ገድለህ ዝቅ ብለህ የተገኘውን መስራት ነው... ካበዛሁት ይቅርታ ያው ከጠቀመህ ብዬ ነው
May 17, 2025