Semuma Ticktok channel kesew lay sigeza mndenw madereg yalbege malet stepun Yemishtelege agegchalehu
May 12, 2025የምትገዛው ቲክቶክ አካውንት ምን አይነት ቪዲዮዎች ናቸው ሲለቀቁበት የነበረው? የሚለውን ማወቅ አለብህ ( ግዴታ ነው ) አንተ መልቀቅ ከምትፈልገው አይዲያ ጋር ተመሳሳይ ሀሰብ ያላቸው ቪዲዮዎች ይለቀቁበት ነበር? የሚለውን ማወቅ አለብህ። የቲክቶክ አካውንቱ በርካታ ፎሎወር ስላለው ብቻ መግዛት የለብህም። ምክንያቱም ቲክቶክ የሚሰራው በኒሽ እና በ አልጎሪዝም ነው። በፎሎወር ብዛት አይደለም። ልትገዛው ያሰብከው ቻነል ያንተ አይነት አይዲያ ቪዲዮ የማይለቀቅበት ከነበረ ቲክቶክ አካውንቱን ፎሎው ያደረጉት ሰዎች አንተ ልትለቅ ካሰብከው አይዲያ ጋር አይመጣጠኑም። በዚህ መሀል አንተ አካውንቱን ገዝተህ ቪዲዮ ስትለቅ ቲክቶክ ለነዚህ ሰዎች ቪዲዮህን ሪኮመንድ አያደርግልህም። ምክያቱም የአካውንቱ ኒሽ ( ይዘት ) ስለተቀየረ። ልክ እንደዚ አስበው። አካውንቱ የኳስ ቪዲዮ ( ቁጥር አንድ ኒሽ ) ብቻ የሚለቀቅበት ነበር እንበል። ይህን አካውንት ፎሎው የሚያደርጉት ሰዎች ኳስ የሚወዱ ናቸው በብዛት። አንተ ፖለቲካ ቪዲዮ ልትለቅ አስበሀል ( ቁጥር ሁለት ኒሽ ) ስለዚህ ቲክቶክ ያንተን ፖለቲክስ ቪዲዮ ለምን ኳስ ለሚወዱ ሰዎች ያቀርብልሀል?? አያቀርበውም። ለዚህ ነው ዩቱብ ውስጥ ስትገባ አንተ የምትወደውን ብቻ የሚያመጣልህ። ይህ አሰራር አልጎሪዝም ይባላል። ስለዚ አንተ ልትለቅ ያሰብከው አይዲያ ከአካውንቱ ሂስትሪ ጋር በጣም ባይቀራረብም ግን ሊመሳሰል ግድ ይላል። ካልሆነ 50ሺህ ፎሎወር ኖሮትም አንተ ምንም ያህል ቪዲዮ ባትለቅ ቲክቶክ ከ 200 ቪው በላይ ላያሳይልህ ይችላል።
May 12, 2025