የመፀሐፍ ቅዱስ ግጭቶች 4) ሰው ወይም እንስሳ፤ የቱ ቀድሞ ስለመፈጠሩ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ሰው የመጨረሻው ፍጥረት እንደሆነ በግልፅ ያስቀምጣል። የተፈረውም ጥንድ ሆነ እንደነበር ጭምር ይነግረናል። ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ደግሞ ከቁጥር 5 ጀምሮ ፍፁም የተለየ የፍጥረት ዘገባ ያደርሰናል። ምዕራፍ 2 ሰው (አዳም ብቻ) ከተፈጠረ በኋላ "የሚመቸውን ረዳት" ለመፍጠር ሲባል እንስሳት እንደተፈጠሩና "እንደ እርሱ ያለ ረዳት" ከነዚህ ስላልተገኘለት ሔዋን ከአጥንቱ እንደተፈጠረች በማስረዳት የፍጥረት ቅደም ተከተሉን አዳም፣ እፅዋት፣ እንስሳት፣ ሔዋን አድርጎ ያስቀምጣል። የታሪክ አጥኝዎች ምዕራፍ አንድ እና ሁለት እስከ ቁጥር 4 በ6ኛው ክፍለ ዘመን ዓዓ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ቄሳዊ የሚባሉ ወገኖች እንደፃፉትና ምዕራፍ ሁለት በ10ኛው ክፍለ ዘመን ዓዓ ያህዌያውያን በሚባሉ ወገኖች እንደተፃፈ፤ በአጠቃላይም የሙሴ አምስት መፃሕፍት ከምርኮ በኋላ ከተለያዩ ምንጮች (አራት አበይት) እንደተዋቀሩ አፃፃፍ፣ ይዘት እንዲሁም የፅሑፎቹን ዘመን ተመርኩዘው ያስረዳሉ። ጥያቄ 1) ምዕራፍ 1 እና 2 አይጋጭም ብሎ የሚያስብ፤ አስረዳ? 2) ይጋጫሉ የሚል፤ እንዲህ ፊትለፊት ያሉ ቅራኔዎች መፀሐፍ ቅዱስ ስናነብ ለምንድን ነው የማይታዩን? አስተውለን የምናልፍ እንበዛለን ወይስ ጭራሽ ትኩረት ያልሰጠን? እነዚህስ ቅራኔዎች ለአንድ አማኝ ለውጥ ያመጣሉ? እንዴት አይነት?
May 12, 2025Go check thise one👉 https://t.me/betremariyamabebaw
May 12, 2025